በሃገር መከላከያ ሚኒስቴር በማዕከላዊ ዕዝ ጠ/መምሪያ 104ኛ ኮር ለ2017 በጀት አመት አገልግሎት የሚውል ከዚህ በታች የተገለፀውን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በሃገር መከላከያ ሚኒስቴር በማዕከላዊ ዕዝ ጠ/መምሪያ 104ኛ ኮር መምሪያ
የጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር 02/2017
በሃገር መከላከያ ሚኒስቴር በማዕከላዊ ዕዝ ጠ/መምሪያ 104ኛ ኮር ለ2017 በጀት አመት አገልግሎት የሚውል ከዚህ በታች የተገለፀውን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
የተለያዩ የፅዳት እና የፅህፈት ማቴሪያል እቃዎች
በዚህም መሰረት በዘርፉ የተሰማሩ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆናቸውን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ ሰርተፍኬት፣ የቫት ሰርተፍኬት እና የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት ያላቸውን ይጋብዛል። ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር መመሪያና ዝርዝር ሰነድ የያዘ 200.00 ብር /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ዘወትር በስራ ሰዓት በደንቢዶሎ ከተማ መብራት ሃይል አካባቢ በሚገኘው የመከላከያ ካምፕ ቅጥር ግቢ ውስጥ የ104ኛ ኮር ግዥ ጊዜያዊ ቢሮ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጊዜ ጀምሮ የጨረታ ሰነድ በመግዛት በቢሮው ወደተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት የምትችሉ መሆኑን እያሳወቅን ጨረታው ሚያዝያ 07/2017 ዓ/ም ከሰዓት 8:30 ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ከሰዓት 9:00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- በ 09 14 84 60 77 መደወል ይችላሉ፡፡
በሃገር መከላከያ ሚኒስቴር በማዕከላዊ ዕዝ ጠ/መምሪያ 104ኛ ኮር መምሪያ
