የኢትዮጵያ ፐልፕና ወረቀት አክሲዮን ማህበር ከዚህ በታች በሎት 1 የተለያዩ ያገለገሉ ና ብረታ ብረቶች በሎት 2 ያገለገሉ የተለያዩ በርሜሎች ፣ ጀሪካኖች እና የመኪና ባትሪዎች በብሔራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
ኢትዮ ፐልፕ እና ወረቀት አክሲዮን ማህበር
ጨረታ ማስታወቂያ
የተለያዩ ብረታ ብረቶች እና ሌሎች ዕቃዎች ሽያጭ
የኢትዮጵያ ፐልፕና ወረቀት አክሲዮን ማህበር ከዚህ በታች በሎት 1 የተለያዩ ያገለገሉ ና ብረታ ብረቶች በሎት 2 ያገለገሉ የተለያዩ በርሜሎች ፣ ጀሪካኖች እና የመኪና ባትሪዎች በብሔራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም ቀጥሎ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ አቅራቢዎች በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋበዛል፡፡
-
የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስተር የአቅራቢዎች ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፡፡
-
ተጫራቾች በዘርፉ መወዳደር የሚያስችል የታደሰ የንግድ ፍቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TN No) ፤ የወቅቱን የታክስ ክሊራንስ እንዲሁም የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
-
ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ (BID BOND) ለሎት 1 (አንድ) 200,000.00 (ሁለት መቶ ሺ ብር) ለሎት 2 በብር 30,000.00 (ሰላሳ ሺህ ብር) ከጨረታ መወዳደሪያ በባንክ በተመሰከረለት ቼክ (C.P.O) ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና (ጋራንቲ) ከኦርጅናል ከቴክኒካል ሠነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል ፡፡
-
ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዱን የማይመለስ በብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) ለእያንዳንዱ ሎት በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡
-
ተጫራች የሚጫረቱበትን ዋጋ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ እስከ ሚያዝያ 09 /2017 ዓ.ም በጨረታ ሰነዱ ላይ ከተገለፀው የመዝጊያ ሰዓት ቀድመው ሰነዱን ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡
-
ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት ለሁሉም ዕቃ ስለዕቃው ዝርዝር ሁኔታ የሚገልፅ ማስረጃ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
-
ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታን ሙሉ በሙሉ ውይንም በከፊል ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
-
የጨረታ ሰነዱ የሚገኝበት እና የሚሸጥበት አድራሻ፡- የኢትዮጵያ ፐልፕና ወረቀት አክሲዮን ማህበር ዋናው መ/ቤት ወንጂ እና አዲስ አበባ አሜሪካን ኤምባሲ ፊት ለፊት በሚገኘው ማስተባበሪያ ቢሮ ሆኖ ጨረታ ሰነድ ማስገባት የሚቻለው እና ጨረታው የሚከፈተው ዋና መሳሪያ ቤት ወንጂ ይሆናል ::
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር +251-022-220-21-18 እና 022-220-17-93
የኢትዮጵያ ፐልፕና ወረቀት አ.ማ
