የጊምቢ ፖሊ ቴክኒክና ሙያ ትምህርት ሥልጣና ኮሌጅ በ2017 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ለሚሰጠው ሥልጠና የሚውል የኤሌክትሪክ ፣ የውሃ ቧንቧ እና የኮንስትራክሽን ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
የጊምቢ ፖሊ ቴክኒክና ሙያ ትምህርት ሥልጠና ኮሌጅ
የጨረታ ማስታወቂያ
የጊምቢ ፖሊ ቴክኒክና ሙያ ትምህርት ሥልጣና ኮሌጅ በ2017 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ለሚሰጠው ሥልጠና የሚውል የኤሌክትሪክ ፣ የውሃ ቧንቧ እና የኮንስትራክሽን ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም የሚከተለውን የጨረታ መሥፈርት የሚያሟሉ ተጫራቾች እንዲወዳደሩ ይጋብዛል፡፡
-
ዕቃዎቹን በጥራት ለማቅረብ የሚያስችል ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፤
-
የዘመኑን ግብር አጠናቀው የከፈሉበትን ማስረጃ የሚያቀርቡ፤
-
የታከስ ከፋይነት /TIN number/ የተመዘገቡ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይ መሆናቸውን ማስረጃ የሚያቀርቡ፤
-
ለጨረታ ማስከበሪያ ጠቅላላ ካቀረቡት ዋጋ 1% በተረጋገጠ ባንክ (CPO) ከጨረታ ሠነድ ጋር ማቅረብ አለባቸው፡፡
-
ተጫራቾች የጨረታውን ሠነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15 ተከታታይ የስራ ቀናት የማይመለስ ብር 100.00 በመክፈል ከኮሌጁ ግዥ እና ፋይናንስ አስተዳደር ሥራ ቢሮ ቁጥር 4 መግዛት ይችላሉ፡፡
-
ተጫራቾች ሠነዱን ቀኑ ሲደርስ በጊምቢ ፖሊ-ቴከኒክና ሙያ ትምህርት ሥልጠና ኮሌጅ ለዚሁ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
-
የጨረታው ማስታወቂያ ከወጣበት በ16ኛው ቀን በስድስት ሰዓት ተዘግቶ በ9፡00 ሰዓት ተጫራቾቹ ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ቀኑ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል፡፡
-
ተጫራቾች በጨረታው አሸናፊ ሆነው ሲቀርቡ ዕቃዎቹን በራሣቸው ማጓጓዣ እስከ ኮሌጁ ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
-
ኮሌጁ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
-
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር፡- 057-7-71-18-72/057-7-71-00-05 በተንቀሳቃሽ ስልክ 09-11-91-67-33/ 09-19-29-40-17 ደውለው ሊረዱ ይችላሉ፡፡
የጊምቢ ፖሊ ቴክኒክና ሙያ ትምህርት ሥልጠና ኮሌጅ
