በደቡብ ኢ/ክ/መንግሥት የጋርዱላ ዞን ፋይናንስ መምሪያ በ2017 በጀት ዓመት የመኪና መለዋወጫ ግዥ እና የመኪና ጥገና የሙያ ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት የጋርዱላ ዞን ፋይናንስ መምሪያ
የጨረታ ማስታወቂያ
በደቡብ ኢ/ክ/መንግሥት የጋርዱላ ዞን ፋይናንስ መምሪያ በ2017 በጀት ዓመት ፡-
1. የመኪና መለዋወጫ ግዥ
2. የመኪና ጥገና የሙያ ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
-
በዘርፉ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድና የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው፤
-
የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ!
-
የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር Tin No ያላቸው!
-
የአቅራቢነት ምዝገባ የምስክር ወረቀት ያላቸው፤
-
የጨረታ ማስከበሪያ 40,000 /አርባ ሺህ ብር/ በጥሬ ገንዘብ ወይም ከታወቀ ባንክ የሚሰጥ የተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ ማቅረብ የሚችሉ፣
-
በትራንስፖርትና መንገድ ልማት የተሰጠ ብቃት ማረጋገጫ ደረጃ 2 /ሁለት/ እና ከዚያ በላይ ማቅረብ የሚችሉ፣
-
ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ከጋርዱላ ዞን ገቢዎች ዩኒት ቢሮ በመቅረብ የማይመለስ 300 /ሦስት መቶ ብር/ በመክፈል መግዛት አለባቸው፡፡
-
ተጫራቾች የገዙትን ሰነድ ኦርጅናልና ኮፒ በማዘጋጀት በሁለት የተለያዩ ፖስታ በማሸግ ኦርጅናሉ ላይ ኦርጅናል ኮፒው ላይ ኮፒ ብሎ በመፃፍ ፊርማና ማህተም በማሳረፍ በዚህ ጋዜጣ ከታወጀበት ቀን ጀምሮ በ16 ተከታታይ ቀናት ወስጥ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀ የጨረታ ሣጥን ውስጥ እስከ 16ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ማስገባት አለባቸው 16ኛው ቀን መደበኛ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይገባል፡፡
-
ጨረታው በዕለቱ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በጋርዱላ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ግዥ ክፍል ከረፋዱ 4፡30 ላይ ይከፈታል፡፡
-
ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸዉ በሰዓቱ ያለመገኘት የጨረታዉን አከፋፈት አያስተጓጉልም፤
-
የጨረታዎቹ አሸናፊዎች ተለይተው ከተገለፀላቸው ከ7 ተከታታይ የሥራ ቀናት በኋላ በ5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ አሸናፊዎች የውል ማስከበሪያ በማስያዝ ዉል መግባት አለባቸው፡፡ ተሸናፊዎች ደግሞ ያስያዙትን የጨረታ ማስከበሪያ መውሰድ ይችላሉ፡፡
-
መምሪያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ ስልክ 0467740344 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ
በደቡብ ሲ/ክ/መንግሥት የጋርዱላ ዞን ፋይናንስ መምሪያ
