Tender Detail

Tender Details


የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ኤጀንሲ በ2017 በጀት ዓመት ለቢሮ አገልግሎት የሚውሉ አላቂ የጽህፈት መሳሪያዎችን፣ ኤሌክትሮኒክ፣ ፈርኒቸር እና የመኪና ዲኮር በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ሙያ ብቃት ማረጋገጫ ኤጀንሲ


 

በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ


የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ኤጀንሲ በ2017 በጀት ዓመት ለቢሮ አገልግሎት የሚውሉ አላቂ የጽህፈት መሳሪያዎችን፣ ኤሌክትሮኒክ፣ ፈርኒቸር እና የመኪና ዲኮር በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

  1. በግብር ከፋይነት ተመዘግበው የአቅራቢነት ሠርተፊኬት ኖሯቸው የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ማቅረብ የሚችሉና የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ሆነው የንግድ ፈቃዳቸውን ያሳደሱ እንዲሁም በጨረታ መሳተፍ የሚችሉበትን የጊዜ ገደብ የሚገልፅ ከሚመለከተው አካል የተሰጠ ማስረጃ በመያዝ የማይመለስ ብር 100.00 በመክፈል ሰነድ በመግዛት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ከሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ሙያ ብቃት ማረጋገጫ ኤጀንሲ ግዥ ፋይናንስ ንብ/አስ/ዳይ/ቢሮ ቁጥር 7 በመቅረብ የጨረታ ሰነድ መግዛት ይችላሉ፡፡

  2. ተጫራቾች የሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ የውል ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ በሕጋዊ ባንክ በተረጋገጠ ቼክ ወይም ሲፒኦ በማዘጋጀት ኦርጅናልና ኮፒ ፖስታዎችን ለየብቻ በታሸገ ኤንቨሎፕ ውስጥ በማድረግ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡ የጨረታ ማስከበሪያ መጠን ከጨረታ መመሪያ ጋር አባሪ ተድርጎ ተያይዟል፡፡

  3. ይህ ጨረታ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት ታሽጎ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ 16ኛው ቀን ቅዳሜና ዕሑድ ወይም በዓል ቀን ከሆነ የጨረታ መክፈቻ ዕለት በተጠቀሰው ሰዓት በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል፡፡

  4. ተጫራቾች በሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ዋጋ ዝርዝር ሰነድ ላይ ስምና አድራሻ በግልፅ በመሙላት በማሕተምና ፊርማ ማረጋገጥ ይኖርባቸዋል፡፡ አንዱ ባቀረበው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡

  5. ተጫራቾች መመሪያ ባለማክበራቸው የሚፈፀም ማንኛውም ስህተት ኃላፊነቱ የተጫራቾች ይሆናል፡፡

  6. ኤጀንሲው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፈል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ ፡-

ሀዋሳ ወደ ሪፈራል በሚወሰደው መንገድ ላይ ከሂል -ሳይድ ሆቴል በስተ-ጀርባ የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ኤጀንሲ ግዥ ፋይናንስ ንብ/አስ/ዳይ/ ቢሮ ቁጥር 7 ሀዋሳ ስለ ጨረታው ተጨማሪ ማብራሪያ ቢያስፈልግዎ በዚህ ስልክ ቁጥር ይደውሉ 0462121129 ወይም 0462121140


ሲዳማ ብ/ክ/መንግስት የሙያ ብቃት ማረጋጋጫ ኤጀንሲ

Save Tender