Tender Detail

Tender Details

  • Company በሸገር ከተማ አስተዳደር የለገጣፎ ለገዳዲ ክ/ከተማ ገቢዎች ጽ/ቤት
  • Address ለገጣፎ ለገዳዲ ክ/ከተማ ደምበል ወረዳ ገዋሳ አካባቢ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0990081623
  • Website
  • Deadline24 Apr 2025, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-04-24 00:00:00
  • Categories Land , House, Building And Warehouse

የለገጣፎ ለገዳዲ ክ/ከተማ ገቢዎች ጽ/ቤት በታክስ ዕዳ የያዘውን ቻይና ኒው ሴንቸር ሪልእስቴት የተባለው ድርጅት በታክስ ባለ እዳ አያያዝ እና አሻሻጥ መመሪያ ቁጥር 18/2012 በተሰጠው ስልጣን መሰረት በማድረግ በግልፅ ጨረታ የሚሸጥ መሆኑን እናስታውቃለን፡፡

በሸገር ከተማ አስተዳደር የለገጣፎ ለገዳዲ ክ/ከተማ ገቢዎች ጽ/ቤት


የጨረታ መስታወቂያ

 

የለገጣፎ ለገዳዲ ክ/ከተማ ገቢዎች ጽ/ቤት በታክስ ዕዳ የያዘውን ቻይና ኒው ሴንቸር ሪልእስቴት የተባለው ድርጅት በታክስ ባለ እዳ አያያዝ እና አሻሻጥ መመሪያ ቁጥር 18/2012 በተሰጠው ስልጣን መሰረት በማድረግ በግልፅ ጨረታ የሚሸጥ መሆኑን እናስታውቃለን፡፡

ከዚህ በታች ያሉትን መስፈርቶችን የምታሟሉት ሁሉ መወዳደር ትችላላችሁ፡፡

1ኛ. የሪል እስቴቱ አድራሻ ለገጣፎ ለገዳዲ ክ/ከተማ ደምበል ወረዳ ገዋሳ አካባቢ፡፡

2ኛ. የቤቶቹ ብዛት 34 ሲሆኑ የጨረታ መነሻ ዋጋ ብር 294,067,876.24 (ሁለት መቶ ዘጠና አራት ሚልየን ስልሳ ሰባት ሺ ስምንት መቶ ሰባ ስድስት ከ 24/100)

3ኛ. የጨረታ ሰነዱን ለመግዛት የምትፈልጉ ለገጣፎ ለገዳዲ ከፍለ ከተማ ገቢዎች ፅ/ቤት ቢሮ ቁጥር 03 ቀርባችሁ የማይመለስ ብር 3000 (ሶስት ሺ) ብር ከፍላችሁ ሰነዱን መግዛት ትችላላችሁ፡፡

4ኛ. ተጫራቾች የጨረታውን መነሻ ዋጋ 10% በባንክ የተረጋገጠ CPO አስቀድሞ ማስያዝ ይኖርባችኋል፡፡

5ኛ. ተጫራቾች የሚገዙበትን ዋጋ በአኃዝና በፊደል በግልፅ ሞልቶ በፖስታ አሽገው በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት አለባችሁ፡፡

6ኛ, ጨረታው የሚቆየው ለ30 ቀን ሲሆን በ31ኛው ቀን ከቀኑ በ7፡30 ተዘግቶ በዚያው ቀን በ8፡30 ላይ በግልፅ ይከፈታል።

7ኛ. ጨረታውን ያሸነፈው ተጫራች በሊዝ አዋጅና መመሪያ ተመዝግቦ የቅድሚያ ክፍያ 20% መክፈል አለበት፡፡

8ኛ ጨረታውን ያሸነፈው ቅድሚያ ያስያዘውን CPO ተጨምሮ በ15 ቀን ቀሪውን አጠናቆ ንብረቱን መረከብ ይችላል፡፡

9ኛ. ጨረታውን ያሸናፈው ለአካባቢው ህብረተሰብ የስራ እድል መፍጠር አለበት፡፡

10ኛ. መስሪያ ቤቱ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገዎት ስ.ቁ. 0990081623 ደውለው መጠየቅ ይቻላል፡፡

 

በሸገር ከተማ አስተዳደር የለገጣፎ ለገዳዲ ክ/ከተማ ገቢዎች ጽ/ቤት

 

Save Tender