የደ/ብርሀን እንጨት ማቀነባበሪያ ኃ/የተ/የግል ማህበር ለሚያመርተው ቬኒር እና ፕላይውድ ጣውላ ግብዓት የሚሆን የባህርዛፍ ግንድ ጫካው ከሚገኝበት ከደ/ብርሃን ወደ ደሴ በሚወስደው መንገድ ከሚገኘው ቀይት ቀበሌ አመር አገር ልዩ ስሙ ቦለድ አካባብ እና ቀይት ቀበሌ ልዩ ስሙ አይሶፌ አካባቢ ደን ሳይት የተቆረጠ ግንድ የሚያመላልሱ ገልባጭ መኪኖችን በዘርፉ የተሰማሩ ባለንብረቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ አሸናፊ ከሆነው ባለንብረት ጋር የኮንትራት ውል በመግባት ግንዱ ተጭኖ እስከሚያልቅ ድረስ ለመከራየት ይፈልጋል።
Debre Birhan Wood Processing Pvt. Ltd (የደ/ብርሀን እንጨት ማቀነባበሪያ ኃ/የተ/የግል ማህበር)
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የደ/ብርሀን እንጨት ማቀነባበሪያ ኃ/የተ/የግል ማህበር ለሚያመርተው ቬኒር እና ፕላይውድ ጣውላ ግብዓት የሚሆን የባህርዛፍ ግንድ ጫካው ከሚገኝበት ከደ/ብርሃን ወደ ደሴ በሚወስደው መንገድ ከሚገኘው ቀይት ቀበሌ አመር አገር ልዩ ስሙ ቦለድ አካባብ እና ቀይት ቀበሌ ልዩ ስሙ አይሶፌ አካባቢ ደን ሳይት የተቆረጠ ግንድ የሚያመላልሱ ገልባጭ መኪኖችን በዘርፉ የተሰማሩ ባለንብረቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ አሸናፊ ከሆነው ባለንብረት ጋር የኮንትራት ውል በመግባት ግንዱ ተጭኖ እስከሚያልቅ ድረስ ለመከራየት ይፈልጋል። በዚህ መሰረት፡-
-
- በዘርፉ የተሰማራና የንግድ ስራ ፈቃዱን ያሳደሰ
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን ነምበር ያላቸው
- የቫት ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትና ሌሎች የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው::
- ተጫራቾች ለሁለቱም የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 40,000.00 /አርባ ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ የከፍያ ትእዛዝ /CPO/ ማስያዝ አለባቸው::
- ተጫራቾች በሚያቀርቡት ሰነድ ላይ ስማቸውን፣ ፊርማቸውንና አድራሻቸውን ማስፈርና የድርጅቱን ማህተም ማድረግ አለባቸው::
- በመጫረቻ ሰነዱ ላይ ምንም አይነት ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም ካለም አንድ ሰረዝ በማድረግ ፊርማቸውን ማስቀመጥ ይኖርባቸዋል።
- ድርጅቱ ከፍያ የሚፈፅመው በቢያጆ ስለሆነ ለመኪናው የሚያስፈልገውን ውጭ የነዳጅ እና ሌሎች ሁሉንም ውጭዎች የሚሸፍነው ባለመኪናው ይሆናል።
- ተጫራቾች ኦሪጅናል የጨረታ ሰነድ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በካምፓኒው የፋይናንስ ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 ቀናት የሚቆይ ስለሆነ ዘወትር በስራ ሰዓት እስከ 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ የጨረታውን ሰነድ ገቢ ማድረግ ይችላሉ።
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4:00 ላይ ታሽጎ 4፡30 ሰዓት ላይ በካምፓኒው የፋይናንስ ቢሮ ውስጥ በይፋ ይከፈታል። ተጫራቾች ባይገኙም ከመከፈት አይታገድም።
- የመክፈቻ ቀኑ የህዝብ በዓል ወይም እሁድ ቀን ከዋለ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።
- አሸናፊ ሆኖ የተመረጠው ተጫራች የውል ማስከበሪያ የሚሆን ገንዘብ በሲፒአ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ብር 100,000.00 /አንድ መቶ ሺህ ብር/ ማስያዝ አለበት።
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0910368437 ደውለው ይጠይቁ፡፡
የደ/ብርሀን እንጨት ማቀነባበሪያ ኃ/የተ/የግል ማህበር
