Tender Detail

Tender Details

  • Company Ethiopian Sugar Industry Group (የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ)
  • Address ሜክሲኮ አካባቢ ከሚገኘው አልሳም ጨለለቅ ህንፃ ፊት ለፊት፣ ፌሊፒስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 220 ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዯጵያ, Phone: +251115500417
  • Websitehttps://etsugar.com/esig/
  • Deadline08 Apr 2025, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-04-08 00:00:00
  • Categories Health Care, Medical Industry , Pharmaceutical Products

የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ በዋናው መ/ቤት እና ወንጂ ለሚገኙ የምርምርና ሥልጠና ዘርፍ ሰራተኞችና ቤተሰቦቻቸው ከዚህ በታች ለተጠቀሱት አገልግሎቶች በዘርፉ የተሰማሩ ድርጅቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ከጨረታው አሸናፊ ተቋማት ጋር ለሁለት አመት የሚቆይ የዱቤ አገልግሎት ግዥ ውል መፈፀም ይፈልጋል፡፡

Ethiopian Sugar Industry Group (የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ)


 

ብሔራዊ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር LP/OT/28/SIG/2017

 

  1. የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ በዋናው መ/ቤት እና ወንጂ ለሚገኙ የምርምርና ሥልጠና ዘርፍ ሰራተኞችና ቤተሰቦቻቸው ከዚህ በታች ለተጠቀሱት አገልግሎቶች በዘርፉ የተሰማሩ ድርጅቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ከጨረታው አሸናፊ ተቋማት ጋር ለሁለት አመት የሚቆይ የዱቤ አገልግሎት ግዥ ውል መፈፀም ይፈልጋል፡፡
  • ሎት-1 የጥርስ ህክምና አገልግሎት ግዥ (አዲስ አበባ ለሚገኙ የህክምና ተቋማት)
  • ሎት-2 የመድሐኒት አቅርቦት አገልግሎት ግዥ (አዳማ ለሚገኙ ተቋማት)
  1. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ብቁ ተጫራቾች ህጋዊ ለ2017 ዓ.ም የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን የሚያረጋግጥ ጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል ከግብር ሰብሳቢው ባለሥልጣን የተሰጠ የታክስ ክሊራንስ በጨረታ መሳተፍ እንዲችል የድጋፍ ምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (Tin No.) ሠርተፍኬት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት ምዝገባ የምስክር ወረቀት እና የመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ወይም ሌላ የሚመለከተው የመንግስት አካል ባዘጋጀው የዕቃ አቅራቢዎች አገልግሎት ሰጪ ዝርዝር ውስጥ መመዝገባቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው::
  2. ብቁ ተጫራቾች በአማርኛ ቋንቋ የተዘጋጀውን የተሟላ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 500.00 (ብር አምስት መቶ) በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ ሂሳብ ቁጥር 1000000888862 ገቢ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጨረታው መክፈቻ ቀን ድረስ ዘወትር በሥራ ሰዓት (ከሰኞ እስከ ዓርብ፣ ከሰዓት በፊት ከ2፡00-6፡00፣ ከሰዓት በኋላ ከ7፡00-11፡00 ቀጥሎ ከተመለከተው አድራሻ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡

የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ

ግዥና ንብረት አስተዳደር መምሪያ

ሚክሲኮ አካባቢ ከሚገኘው አልሳም ጨለለቅ ህንፃ ፊት ለፊት፣

ፊሊፕስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 220

ስልክ ቁጥር +251 11 5 50 04 17 ወይም 011 5 51 62 71

አዲስ አበባ፣ኢትዮጵያ

  1. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ በማሸግ ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። ጨረታው በጨረታው መክፈቻ ላይ መገኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በተራ ቁጥር 3 በተገለፀው አድራሻ መጋቢት 30 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡ ዘግይቶ የሚቀርብ የመጫረቻ ሰነድ ተቀባይነት የለውም::
  2. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሎት-- 1 ብር 25,000.00 (ሃያ አምስት ሺህ ብር) እንዲሁም ለሎት-2 ብር 15,000.00 (አስራ አምስት ሺህ ብር) በባንክ የተመሠከረለት የክፍያ ማዘዣ (CPO) ከቴክኒክ መጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  3. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትናው ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለዘጠና (90) ቀናት ፀንቶ የሚቆይ መሆን ይኖርበታል፡፡
  4. የጨረታ ዋጋ ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለስልሳ (60) ቀናት ይሆናል።
  5. ግሩፑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

 

የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ

 

Save Tender