Tender Detail

Tender Details

  • Company Auction Ethiopia S.C. (ኦክሽን ኢትዮጵያ አክሲዮን ማኅበር)
  • Address Bole Atlas, around European Union, Tomoka Bldg, 3rd flr, Suit - 301 Addis Ababa, Ethiopia, Phone: 09-05-11-5511
  • Websitehttps://auction.et/home
  • Deadline22 Apr 2025, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-04-22 00:00:00
  • Categories Land , House, Building And Warehouse , Materials , Vehicle

ሳባና ሪዞርት በላንጋኖ የሚገኘውን 60000sqm ያረፈ ሪዞርት እና በውስጡ የሚገኙ ንብረቶችን ባሉበት ቦታና ሁኔታ በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ለመሸጥ አቅርቧል።

Auction Ethiopia S.C. (ኦክሽን ኢትዮጵያ አክሲዮን ማኅበር)


 

የጨረታ ማስታወቂያ

 

ሳባና ሪዞርት በላንጋኖ የሚገኘውን 60000sqm ያረፈ ሪዞርት እና በውስጡ የሚገኙ ንብረቶችን ባሉበት ቦታና ሁኔታ በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ለመሸጥ አቅርቧል፤ ስለሆነም ከዚህ በታች የተገለጹትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ማንኛውም ሕጋዊ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡

ማሳሰቢያ፡- ጨረታው የሚከናወነው ሙሉ በሙሉ ኦክሽን ኢትዮጵያ አክሲዮን ማኅበር በፈጠሩት የጨረታ ሲስተም መተግበሪያ auction.et መሰረት መሆኑን እየገለጽን መስፈርቶቹ እንደሚከተለው ቀርቧል፡-

  1. በጨረታው የሚወዳደሩ ተጫራቾች ማንነታቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ወይም የታደሠ መታወቂያ ሊኖራቸው ይገባል፡፡
  2. ስለጨረታው አካሄድ እና ንብረቶች ዝርዝር መግለጫ የያዘውን ሰነድ የኦክሽን ኢትዮጵያ ፕላትፎርም ላይ ከንብረቶቹ መግለጫ ስር ተያይዞ የሚገኝ ስለሆነ በነጻ አውርደው መመልከት ይችላሉ።
  3. ተጫራቾች የጨረታው ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ኦክሽን ኢትዮጵያ አክሲዮን ማኅበር ጋር ቀጠሮ በማስያዝ ዘወትር በሥራ ቀናት ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 10፡00 ሰዓት ንብረቶቹ በሚገኙበት ቦታ በመገኘት መመልከት ይቻላል፡፡
  4. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ በጨረታ ሰነዱ ላይ በተቀመጠው መሰረት ሲሆን ፣ 1,000,000 ብር በማሰራት የኦክሽን ኢትዮጵያ መተግበሪያ ላይ የሚጫረቱበትን ዋጋ ማስገባት ይችላሉ፡፡
  5. ጨረታው ከ15/7/2017 እስከ 14/8/2017 ዓ.ም ድረስ ይካሄዳል፡፡ ስለሆነም ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎች የጨረታውን ሂደት በቀጥታ (online) መከታተል ይችላሉ።
  6. ተጫራቾች የኦክሽን ኢትዮጵያን መተግበሪያ ከአፕ ስቶር ወይም ፕሌይ ስቶር (Auction Ethiopia) ብለው በማውረድ ወይም (auction.et) ላይ መመዝገብ እና መጫረት ይችላሉ።
  7. በጨረታው አሸናፊ ለምትሆኑ ተጫራቾች ለወደፊት አሸናፊነታችሁ በሚገለፅላችሁ ቀን ጀምሮ የሚቆጠር አምስት ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ የአሸነፋችሁበትን ዋጋ ሙሉውን ክፍያ ለወደፊት በምናሳውቃችሁ በተቋማችን ሂሳብ ቁጥር ገቢ በማድረግ የሽያጭ ውል ስምምነት መፈጸም ግዴታ ይኖርባቸዋል፤ ሆኖም ግዴታቸውን የማይወጡ ተጫራቾች ለወድድር ያስያዛችሁት የጨረታ ማስከበሪያ ሲ.ፒ.ኦ. ለድርጅቱ ገቢ ይደረጋል፡፡
  8. ከላይ የተጠቀሰውን እና በጨረታ ሠነዱ ላይ የተቀመጡ መመሪያዎችን ያላሟላ ተጫራች ከጨረታው ውድቅ/ሊሰረዝ ይችላል፡፡
  9. ሳባና ሪዞርት ጨረታውን ለመቀበል ወይም ላለመቀበል የሚችል ሲሆን በማንኛውም ጊዜ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  10. የኦክሽን ኢትዮጵያን መተግበሪያ በተመለከተ የጥሪ ማዕከሉን ለማግኘት በአጭር የስልክ መስመር 9164 ወይም 09-05-11-5511/ 011-666-8828 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።

 

ኦክሽን ኢትዮጵያ አክሲዮን ማኅበር

 

Save Tender