የባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ በሚደነግገው አዋጅ ቁጥር 721/2004 አንቀፅ 8 ንዑስ አንቀፅ 1 መሰረት በ2017 በጀት ዓመት የከተማ መሬት ልዩ የሊዝ ጨረታ ለንግድ አገልግሎት /ለሞል፤ ለሞልና አፓርትመንት ባለ አራት ኮከብ እና በላይ ለሆኑ ሆቴሎች/ የሚሆኑ 10 (አስር) ቦታዎችን በልዩ ጨረታ ለተጫራቾች ማስተላለፍ ይፈልጋል፡፡
የባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ
የሊዝ ጨረታ ማስታወቂያ
1021/07/2017
የባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ በሚደነግገው አዋጅ ቁጥር 721/2004 አንቀፅ 8 ንዑስ አንቀፅ 1 መሰረት በ2017 በጀት ዓመት የከተማ መሬት ልዩ የሊዝ ጨረታ ለንግድ አገልግሎት /ለሞል፤ ለሞልና አፓርትመንት ባለ አራት ኮከብ እና በላይ ለሆኑ ሆቴሎች/ የሚሆኑ 10 (አስር) ቦታዎችን በልዩ ጨረታ ለተጫራቾች ማስተላለፍ ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም፡-
- መጫረት የሚፈልግ ማንኛውም ግለሰብ ወይም ድርጅት ይህ ማስታወቂያ በአማራ ቴሌቪዥን ከተነገረበት ቀን ጀምሮ ባሉት 20 /ሀያ/ የስራ ቀናት ውስጥ የማይመለስ ብር 1000 (አንድ ሺህ ብር) በመክፈል ቀበሌ 08 ከአዲሱ የከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ ቢሮ ቁጥር 310 በመምጣት የጨረታ ሰነድ መግዛት ይችላል፡፡
- የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ጊዜ ሁሉም ተጫራች በተገኙበት በመጨረሻው ቀን ማለትም በ20ኛው ቀን እስከ 11፡00 ሰዓት ብቻ ለዚህ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በቢሮ ቁጥር 310 ይሆናል።
- ጨረታው የሚዘጋው በ20ኛው ቀን በ 11፡00 ሰዓት ይሆናል፡፡
- ጨረታው የሚከፈተው ጨረታው ከተዘጋበት ቀን ቀጥሎ ባለው የስራ ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት ጀምሮ ሁሉም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሲሆን ጨረታው የሚከፈትበትን ቦታ በተመለከተ በውስጥ ማስታወቂያ የሚገለጽ ይሆናል፡፡
- ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ በመምሪያው የውስጥ ማስታወቂያ መለጠፊያ ሰሌዳ ፧ በድረ-ገፅ www.ambioud.gov.et/www.amhara.gov.et ማግኘት ይቻላል፡፡
- መስሪያ ቤቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ
