Tender Detail

Tender Details

  • Company በመከላከያ መሃንዲስ ዋና መምሪያ በኮንስትራክሽን መምሪያ የጃንሜዳ ባህር ኃይል ጠቅላይ መምሪያ ዋና ቢሮ ፕሮጀክት(Defense Engineer General Department Construction Department Janmeda Navy General Department General Office Project)
  • Address Addis Ababa, Ethiopia, Phone: 09 66 93 69 71
  • Website
  • Deadline08 Apr 2025, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-04-08 00:00:00
  • Categories Electrical And Electromechanical , Generators , Vehicle Battery , Sanitary Ware

ያገለገሉ ዕቃዎችን ሽያጭ ማስታወቂያ የግዥ መ/ቁጥር መ/መ/ሃ/መ/ግ/ጨ/01/2017 ዓ/ም የመከላከያ መሃንዲስ ዋና መምሪያ ከዚህ በታች የተጠቀሱትን ያገለገሉ እቃ ማንኛውም ዜጋ የታደሰ መታወቂያ እና አድራሻ ያለው ሁሉ ድርጅቶችም ሆነ በግል አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

በመከላከያ መሃንዲስ ዋና መምሪያ በኮንስትራክሽን መምሪያ የጃንሜዳ ባህር ኃይል ጠቅላይ መምሪያ ዋና ቢሮ ፕሮጀክት(Defense Engineer General Department Construction Department Janmeda Navy General Department General Office Project)


 

ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

 

ያገለገሉ ዕቃዎችን ሽያጭ ማስታወቂያ የግዥ መ/ቁጥር መ/መ/ሃ/መ/ግ/ጨ/01/2017 ዓ/ም የመከላከያ መሃንዲስ ዋና መምሪያ ከዚህ በታች የተጠቀሱትን ያገለገሉ እቃ ማንኛውም ዜጋ የታደሰ መታወቂያ እና አድራሻ ያለው ሁሉ ድርጅቶችም ሆነ በግል አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል። በዚህም መሰረት

የተለያየ መጠን ያላቸው ጀነሬተሮች ሎት 01

ሰመር ሰብል ፓምፕ እና የውሃ ማጣሪ ማሽን ሎት 02

የመኪና ባትሪዎች ሎት 03

አሮጌ ቁርጥራጭ ብረት ሎት 04

የተለያየ መጠን ያላቸው ፓምፖች ሎት 05

የተለያዩ የሳኒተሪ እቃዎች ሎት 06

የተለያዩ ሲቪል ዎርከ እቃዎች ሎት 07

የተለያዩ የኤልክትሪክ እቃዎች ሎት 08

የጀነሬተር የጭቃ መከላከያ ና የተቃጠለ ዘይት ሎት 09

በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል። በመሆኑም በጨረታ የሚገዛው ዋጋ 2% (ሁለት ፐርሰንት) ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማስያዣ (CPO) ማስያዝ የሚችል መሆን ይኖርበታል። ከላይ የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ እና የሚመለከታቸው ማስረጃዎችን ቅጂ (ኮፒ) ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ የሚችሉ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ መዝጊያው እለት ድረስ ዘወትር በስራ ቀናት ከ2፡30 ሰዓት እስከ 10፡30 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ በመከላከያ መሃንዲስ ዋና መምሪያ ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ 12 በመቅረብ ለዚህ ጨረታ በአማሪኛ የተዘጋጀውን ዝርዝር መረጃ የያዘ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00 በመክፈል ገዝተው መወዳደር ይችላል።

የጨረታ ሳጥኑ በመሃንዲስ ዋና መምሪያ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን የሰነድ ማስገቢያ ጊዜም የጨረታ ሰነድ ከገዙበት ቀን ጀምሮ እስከ መዝጊያው እለት ይሆናል። የመክፈቻው ቦታ በመሃንዲስ ዋና መምሪያ መክፈቻው 30/07/2017 ከጠዋቱ 4፡00 ተዘግቶ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል ።

  • የጨረታው ሳጥኑ ከታሸገ በኋላ ዘግይቶ የሚደርስ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም።
  • መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ፡ -አዲስ አበባ ጃን ሜዳ ባህረ ጥምቀቱ ፊት ለፊት ስልክ ቁጥር 0919127207

 

የመከላከያ መሃንዲስ ዋና መምሪያ

 

Save Tender