በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሥልጤ ዞን የወራቤ ከተማ አስተዳደር ጤና ጽ/ቤት የአልከሶ ጤና ጣቢያ አጥር ግንባታ በዘርፉ የተሰማሩ ደረጃ 9 የግንባታ ማኅበራትን በጨረታ አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል፡፡
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት የስልጤ ዞን የወራቤ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሥልጤ ዞን የወራቤ ከተማ አስተዳደር ጤና ጽ/ቤት የአልከሶ ጤና ጣቢያ አጥር ግንባታ በዘርፉ የተሰማሩ ደረጃ 9 የግንባታ ማኅበራትን በጨረታ አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም፡-
- በመስኩ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣
- የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው፣
- የቲን ነምበር ያላቸው፣
- የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ፣
- በመንግሥት ግዥ ለመሳተፍ የአቅራቢነት ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ፣
- የጨረታ ዋስትና ብር 10,000 በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ የሚችሉ፤
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከወራቤ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት በመምጣት የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 300 /ሶስት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል መግዛት የምትችሉ መሆኑን እያሳወቅን፤ የጨረታ ሰነዱን አንድ ኦርጅናልና ሁለት ፎቶ ኮፒ ለየብቻ በታሸገ ፖስታ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከታተመበት ዕለት ጀምሮ ባሉት 21 /ሀያ አንድ/ ተከታታይ ቀናት በኋላ ባለው የሥራ ቀን ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ድረስ በጽ/ቤቱ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፣ የጨረታ ሳጥኑ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ ከጠዋቱ 4፡30 መገኘት በሚፈልጉ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
ማሳሰቢያ፡-
መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው:: የተሞላው ዋጋ መግለጫ ካልተሰጠበት ከነቫት ተደርጎ ይወሰዳል፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 046 771 02 11 ይደውሉ
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በስልጤ ዞን የወራቤ ከተማ አስተደዳር ፋይናንስ ጽ/ቤት
