በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ሙግር ሲሚንቶ ፋብሪካ ለፕሪንተር እና ለኮፒ ወረቀት እና ቦክስ ፋይል ከዚህ ቀጥሎ በቀረበው ዝርዝር መሠረት የሚያቀርቡ ተጫራቾችን በሀገር ውስጥ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
Chemical Industry Corporation Mugher Cement Factory (በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ)
የጨረታ ማስታወቂያ
የሀገር ውስጥ ግልፅ ጨረታ ቁጥር ሙሲፋ/46/2017
በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ሙግር ሲሚንቶ ፋብሪካ ለፕሪንተር እና ለኮፒ ወረቀት እና ቦክስ ፋይል ከዚህ ቀጥሎ በቀረበው ዝርዝር መሠረት የሚያቀርቡ ተጫራቾችን በሀገር ውስጥ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
|
ተ.ቁ |
አይነት |
መለኪያ |
ብዛት |
አይነት |
|
1 |
ወረቀት |
በቁጥር |
3940 |
የፕሪንተር እና ኮፒ |
|
2 |
ቦክስ ፋይል |
በቁጥር |
3300 |
ሰማያዊ |
ስለዚህ የንግድ ምዝገባና ሕጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው ፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉና የተጨማሪ እሴት ታክስ እና የታክስ ከፋይ ተመዝጋቢ የሆኑ የተጠቀሱትን ሰነዶች ኮፒ በመያዝ ተጫራቾች የማይመለስ ብር 115.00 (አንድ መቶ አሥራ አምስት ብር) ከነቫቱ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን አዲስ አበባ በቅሎ ቤት አካባቢ ጋራድ ህንፃ ቢሮ ቁጥር 432- 3-8 ከሚገኘው የግዥ መምሪያ ቢሮ እየቀረቡ መግዛት ይችላሉ፡፡ ተጫራቾች ብር 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ) የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ ስም በባንክ በተረጋገጠ ቼክ (C.P.O) ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ ባንክ ጋራንቲ ከቴክኒክ ዶክመንቶቹ ጋር በማያያዝ ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ሚያዝያ 14 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ድረስ በሰም በታሸገ ኤንቨሎኘ የጨረታ ሰነዳቸውን አዲስ አበባ በሚገኘው በግዥ መምሪያ ቢሮ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።ጨረታው በዕለቱ ሚያዝያ 14 ቀን 2017 ዓ.ም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት በግዥ መምሪያ ቢሮ ይከፈታል፡፡ ፋብሪካው ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ስልክ 0114420216
ፋክስ 0114420688
በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ
