ድርጅታችን አቢሲኒያ ትራንስፖርት አ.ማ የማህበሩን የቀጣይ 3 (ሶስት) አመታት የሂሳብ ስራውን ብቃት ባላቸው አዲተሮች የሒሳብ ምርመራ በጨረታ አወዳድሮ ለማስራት ይፈልጋል፡፡
Abyssinia Transport Solution (አቢሲኒያ ትራንስፖርት አ.ማ)
የሒሳብ ምርመራ አገልግሎት የጨረታ ማስታወቂያ
ድርጅታችን አቢሲኒያ ትራንስፖርት አ.ማ የማህበሩን የቀጣይ 3 (ሶስት) አመታት የሂሳብ ስራውን ብቃት ባላቸው አዲተሮች የሒሳብ ምርመራ በጨረታ አወዳድሮ ለማስራት ይፈልጋል፡፡ በዚህ መሰረት በጨረታው ለመሳተፍ የሚችሉ የአዲት አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶች የሚከተሉትን መስፈርቶች በማሟላት እንዲወዳደሩ ተጋብዘዋል፡፡
- በኢትዮጵያ ሒሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ መስሪያ ቤት የተመዘገበና የታደሰ የኦዲት ስራ ፍቃድ ያላቸው እንዲሁም ቢያንስ ለ5 (አምስት) ዓመት የኦዲት ድርጅት ከፍተው የሰሩ፣
- የንግድ ስራ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ፣
- አገልግሎት ለሚሰጡበት ከሚጠይቁት ጠቅላላ ዋጋ ላይ ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚሆን 3% በባንክ የተመሰከረለት ቼክ ወይም CPO ወይም በጥሬ ገንዘብ የተከፈለበት ደረሰኝ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ የሚችሉ፤
- የቴክኒካልና የፋይናንሺያል ጨረታ መወዳደሪያ ሰነዶቻቸውን በተናጠል በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ መጋቢት 24 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 10፡00 ድረስ በአክሲዮን ማህበሩ ዋና መስሪያ ቤት ፋይናንስ ዋና ከፍል በመገኘት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልጉ የኦዲት አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶች ለጨረታ የሚያስፈልጓቸውን ሰነዶችና መረጃዎች በአከሲዮን ማህበሩ በአካል ተገኝተው ወይም በስልክቁጥር- 011-4-43-14-16 ደውለው መረዳት ይችላሉ፤
ማሳሰቢያ፡-
አክሲዮን ማህበሩ የተሻለ መንገድ ካገኘ በጨረታው የማይገደድ ሲሆን በደረቅ ጭነት ትራንስፖርት ዘርፍ ላይ የተሰማሩ አክሲዮን ማህበራትንም ሆነ ድርጅቶችን ኦዲት ያደረጉ ተጫራቾች የበለጠ ይበረታታሉ፤ የጨረታው አሸናፊ እንደታወቀ ሌሎች ተጫራቾች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ከጨረታው መዝጊያ በኋላ ባሉት 7 (ሰባት) ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል፤
አድራሻ፡- ሳሪስ የገበያ ማዕከል ዝቅ ብሎ ወይም ዩኒቨርሳል ቆዳ ፋብሪካ ፊት ለፊት
አቢሲኒያ ትራንስፖርት አ.ማ
