በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጉራጌ ዞን የነደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2017 በጀት ዓመት በመደበኛ በጀት ለሚያሰራው ከአረዳ እስከ ጅማ ድረስ ያለው የመንገድ ግንባታ ስራ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ ሀገር አቀፍ ግልፅ
ጨረታ ማስታወቂያ መለያ ቁጥር GGWW/0027/2017
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጉራጌ ዞን የነደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2017 በጀት ዓመት በመደበኛ በጀት ለሚያሰራው ከአረዳ እስከ ጅማ ድረስ ያለው የመንገድ ግንባታ ስራ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም ተጫራቾች ፦
- የዘመኑን ንግድ ፍቃድ ያሳደሱ የቫት እና ቲን ነምበር ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚገልፅ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የመወዳደሪያ ደረጃቸውም GC/RC ደረጃ 7 እና ከዛ በላይ የሆኑ ተቋራጮች::
- በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልጉ ተወዳዳሪዎች የሚገዙት ጨረታ ሰነዱን ጠቅሰው በማመልከቻ ሲጠይቁ ተወካዮች ከሆነ ከድርጅቱ ህጋዊ ውከልና ይዘው መምጣት አለባቸው::
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 21ኛው ተከታታይ ቀናት እስከ 8፡00 ሰዓት ድረስ የማይመለስ ብር 300 /ሶስት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል የጨረታውን ሰነድ መሀል አምባ ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 03 ድረስ በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ለ90 ቀናት ፀንቶ የሚቆይ ብር 100000 (መቶ ሺህ ብር) በገ/ጉ/ወ/ወ/ፋይናንስ ፅ/ቤት ስም ማሰራት አለባቸው::
- ተጫራቾች የጨረታውን ቴክኒካል እና ፋይናንሻል ዶክመንት ሲያቀርቡ ሀ/ ለቴከኒካል ዶክመንት አንድ ኦርጅናል እና ሁለት ፎቶ ኮፒ በማድረግ ቴክኒካል በሚል በመለየት ለ/ ለፋይናንሻል ዶክመንት አንድ ኦርጅናል እና ሁለት ፎቶ ኮፒ በማድረግ ፋይናንሻል በሚል በመለየት በማሸግ ከላይ በተጠቀሰው የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ/ ከባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ከቴክኒካል ኦርጅናል ዶክመንቱ ጋር በማድረግ በማሸግ ቴክኒካል ዶክመንት በሚል በመለየት ይህ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ባሉት 21 (ሀያ አንድ) ተከታታይ ቀናት መሀል አምባ የገ/ጉ/ወ/ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 03 ድረስ በመምጣት ለጨረታ አገልግሎት በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታው ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ21ኛው ተከታታይ ቀን በ8፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚያኑ ቀን በ8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- በጨረታው ሰነድ ላይ ምንም አይነት ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም።
ማሳሰቢያ:-
- በአፈፃፀም ምክንያት ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸው ድርጅቶች መወዳደር አይችሉም፡፡
- በወረዳው ውስጥ ሁለትና ከዚያ በላይ ፕሮጀክት ይዞ ስራውን ያልጨረሰ ተጫራች መወዳደር አይችልም።
- ተጫራቾች ሰነድ ለመግዛት ሲመጡ ከአሰሪው መስሪያ ቤት የሳይት ምልከታ ማየታቸውን የሚገልጽ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉና ።
- ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በዓል ወይም ቅዳሜና እሁድ ከሆነ ወደሚቀጥለው የስራ ቀን ይዘዋወራል።
- አሸናፊው ድርጅት ቅድመ ክፍያ ሳይወስድ /ሳይጠይቅ ስራ መጀመር የሚችል።
ለበለጠ መረጃ የገ/ጉ/ወ/ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ
ስልክ ቁጥር፡- 0113360162/146 ይደውሉ
የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት
