Tender Detail

Tender Details

  • Company Ethiopian Insurance Corporation (የኢትዮጵያ መድን ድርጅት)
  • Address Lagar, Ras Mekonen Ave, Addis Ababa, Ethiopia, Phone: 011-551 24 00
  • Websitehttps://eic-et.com/branches/
  • Deadline07 Apr 2025, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-04-08 00:00:00
  • Categories Vehicle , Vehicle Battery

የኢትዮጵያ መድን ድርጅት አደጋ ደርሶባቸው ለደንበኞቹ ሙሉ የመድን ካሣ ከፍሎ የተረከባቸውን ቀረጥ የተከፈለባቸው ልዩ ልዩ ተሽከርካሪዎች፣ ልዩ ልዩ የተሽከርካሪ ውጫዊና የውስጥ አካላት፤ የተለያዩ ብረታ ብረቶችን በጨረታ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

Ethiopian Insurance Corporation (የኢትዮጵያ መድን ድርጅት)


 

የጨረታ ማስታወቂያ

 

የኢትዮጵያ መድን ድርጅት አደጋ ደርሶባቸው ለደንበኞቹ ሙሉ የመድን ካሣ ከፍሎ የተረከባቸውን፡-

  • ቀረጥ የተከፈለባቸው ልዩ ልዩ ተሽከርካሪዎች፣
  • ልዩ ልዩ የተሽከርካሪ ውጫዊና የውስጥ አካላት፤
  • የተለያዩ ብረታ ብረቶችን በጨረታ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

ማንኛውንም የስም ማዛወሪያ፣ ተጨማሪ የጉምሩከ ቀረጥ፣ ግብር፣ እሴት ታክስና ሌሎች ወጪዎች ቢኖሩ ከፍሎ በጨረታ ለመግዛት የሚፈልግ ሁሉ ቃሊቲ ክራውን ሆቴል በስተጀርባ በሚገኘው የድርጅቱ ሪከቨሪ ቴከኒከ ማዕከል በመገኘት ከመጋቢት 15 ቀን 2017 ጀምሮ እስከ መጋቢት 29 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ በመመልከትና የጨረታ ማስከበሪያ በኢትዮጵያ መድን ድርጅት /Ethiopian Insurance corporation/ ስም በተሰራ ሲፒኦ በማስያዝ መጫረት ይችላሉ፡፡

ሀ/ የዕቃ ማስያዣ:- የጨረታ መነሻ ዋጋ 20 በመቶ ሲሆን ዝቅተኛ የዕቃ ማስያዣ ብር 1000 ነው::

ለ/ የተሸከርካሪ ማስያዣ

የጨረታ መነሻ

እሰከ ብር 50,000

20 በመቶ

ከብር 50,001.00

እስከ ብር 100,000.00

ብር 15,000.00

ከብር 100,001.00

እስከ ብር 200,000.00

ብር 25,000.00

ከብር 200,001.00

እስከ ብር 300,000.00

ብር 37,000.00

ከብር 300,001.00

እስከ ብር 400,000.00

ብር 50,000.00

ከብር 400,001.00

እስከ ብር 500,000.00

ብር 60,000.00

ከብር 500,001.00

እስከ ብር 800,000.00

ብር 75,000.00

ከብር 800,001.00

ብር በላይ

ብር 100,000.00

 

ተጫራቾች የሚገዙበትን ዋጋ ከተጨማሪ እሴት ታክስ በፊት በመሙላት የጨረታውን ሠነድ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ መጋቢት 29 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡30 ሰዓት ጀምሮ እስከ ቀኑ 10፡00 ሰዓት ድረስ ለገሀር በሚገኘው ዋናው መ/ቤት ለዚሁ በተዘጋጀው ሣጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው መጋቢት 30 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ቃሊቲ በሚገኘው በሪከቨሪ ቴክኒክ ማዕከል ይከፈታል፡፡ በጨረታው ተሸናፊ ለሚሆኑ ተወዳዳሪዎች የጨረታ ማስከበሪያ ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ከሁለት የሥራ ቀናት በኋላ ተመላሽ የሚደረግ ሲሆን፣ ለአሸናፊዎች ግን ሂሣቡ በገዙት ንብረት ላይ የሚታሰብ ሆኖ፣ የገዙትን ንብረት ተጫራቾች መክፈል ከጀመሩበት ቀን ጀምሮ በ10 ቀናት ጊዜ ውስጥ ክፍያ አጠናቀው ንብረቱን ባይረከቡ ለጨረታ ተሳትፎ ያስያዙት ገንዘብ በመቀጫ መልክ ለድርጅቱ ገቢ ሆኖ ጨረታው ይሰረዛል፡፡ ክፍያ ፈፅመው ንብረቶቹን በተገለፀው ጊዜ የማያነሱ ተጫራቾች የጥበቃ ወጪ በቀን ብር 150 (አንድ መቶ ሃምሳ ብር) ይከፍላሉ፡፡

ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ያሸነፈውን ተሽከርካሪም ሆነ ቁሳቁስ ባለበት ሁኔታ በአንድ ጊዜ ማንሳት አለበት፡፡ ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

 

ለበለጠ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር፡- 011-4-39-25-89 እና 011-4-39-25-45 መጠየቅ ይቻላል፡፡

 

የኢትዮጵያ መድን ድርጅት

 

 

Save Tender