Tender Detail

Tender Details


በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የሰሜን ምዕራብ ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ ለ2017 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ አይነት ንብረቶችን /እቃዎችን/ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የሰሜን ምዕራብ ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ


 

ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር፡- A-05/2017

 

በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የሰሜን ምዕራብ ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ ለ2017 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ አይነት ንብረቶችን /እቃዎችን/ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም በዚህ ጨረታ መወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች አግባብ ያለው የዘርፉ የታደሰ የዘመኑ የንግድ ፈቃድ፤ የምዝገባ የምስክር ወረቀት፤ የቫት ሰርተፊኬት፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ሰርተፊኬት /TIN No/፤ ጨረታ እንዲሳተፉ ከገቢዎች የተሰጠ ደብዳቤ እና የወሩ መጨረሻ ለመንግስት ቫት ሪፖርት የተደረገበት ማስረጃ ሁሉም ማስረጃዎች /ንግድ ፈቃዶች/ በተናጠል ኮፒ መደረግ አለባቸው፡፡ የአንዱን ጨረታ ሰነድ ዋጋ የማይመለስ ብር 250.00 /ሁለት መቶ ሃምሳ ብር ብቻ/ በመክፈል ዘወትር በስራ ሰዓት ባህር ዳር ከተማ በሰ/ምዕ/ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ መኮድ ካምፕ ግዥ ቢሮ ቁጥር፡-02 በመምጣት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ14 ተከታታይ ቀናት ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡ የጨረታ ማስከበሪያ /BID BOND: CPO ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ አለበት/GARANTE/::

  1. የተለያዩ አይነት የፅህፈትና የስልጠና መርጃ እቃዎች ብር 23,561.47
  2. የተለያዩ አይነት የታካሚ ቀለብ ብር 61,653.28
  3. የተለያዩ አይነት የፅዳት እቃዎች ብር 108,950.72
  4. የተለያዩ አይነት የዳቦ ማሽንና ጀነሬተር መለዋወጫ እቃዎች ብር 13,134.00
  5. የተለያዩ አይነት የተሽከርካሪ አላቂ መለዋወጫ እቃዎች ብር 18,235.55
  6. የተለያዩ አይነት የግንባታ እቃዎች ብር 97,664.71

ጨረታው ከረቡዕ 10/07/2017 እስከ ማክሰኞ 23/07/2017 ዓ.ም ከቀኑ 10፡00 ሰዓት የጨረታ ሰነድ ተሸጦ የሚያልቅበት ቀን ሲሆን ረብዕ 24/07/2017 ዓ.ም በ3፡30 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን በ3፡45 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በባህር ዳር ከተማ በሰ/ምዕ/ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ መኮድ ዋናው ቢሮ አዳራሽ ወስጥ ይከፈታል፡፡

  • መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
  • በጨረታው ላይ ያልተገለፁ ዝርዝር ሁኔታዎችን ከፈለጉ ቅፅ 1 ጥር 1998 ዓ.ም በሃገር ውስጥ ለሚፈፀሙ እቃዎችና ተዛማች አገልግሎቶች ግዥ የሚውል መደበኛ የጨረታ ሰነድ ከገንዘብና የኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር የመንግስት ግዥ ኤጀንሲ ድረ-ገፅ ላይ ወይም ከመስሪያ ቤቱ በሚገዙት መደበኛ የጨረታ ሰነድ ማየት ይችላሉ፡፡

ስ.ቁ:- 058-3-21-65-82/058-3-21-28-92/09-87-39-48-58

 

የሰ/ምዕ/ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ

 

Save Tender