በገቢዎች ሚኒስቴር የአዳማ ቅ/ጽ/ቤት በአዳማ እና በቢሾፍቱ ለሚገኙ ሰራተኞች የትራንስፖርት ሰርቪስ አገልግሎት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የገቢዎች ሚኒስቴር አዳማ ቅ/ጽ/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር አገ 11/2017
በገቢዎች ሚኒስቴር የአዳማ ቅ/ጽ/ቤት በአዳማ እና በቢሾፍቱ ለሚገኙ ሰራተኞች የትራንስፖርት ሰርቪስ አገልግሎት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ እና ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ በዘርፉ የተሰማሩ አቅራቢዎች እንዲወዳደሩ ይጋብዛል፡፡
- አገልግሎቱ የሚቀርበው በአዳማ እና በቢሾፍቱ ከተማ አስተዳደር ውስጥ ሲሆን ዝርዝሩን ከጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች በትራንስፖርት የሥራ ዘርፍ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፣ በአቅራቢዎች ዝርዝር ድረ-ገጽ የተመዘገቡ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ የምስከር ወረቀት እና የቫት ሰርተፍኬት ያላቸው እንዲሁም የዘመኑን የሥራ ግብር የከፈሉና ግዴታቸውን የተወጡ መሆኑን የሚያረጋግጥ የድጋፍ ደብዳቤ ከሚመለከተው የገቢ ሰብሳቢ መስሪያ ቤት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው::
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ቀናት ውስጥ የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን አዳማ የቀድሞው ጅንአድ ፊት ለፊት የሚገኘው የገቢዎች ሚኒስቴር አዳማ ቅ/ጽ/ቤት ህንፃ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 403 በመምጣት መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3:45 በፊት ለጨረታው የሚያስፈልግ ማንኛውንም የጨረታ ሰነድ በቅ/ጽ/ቤቱ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት አለባቸው:: በመሆኑም የጨረታ ሳጥኑ ከታሸገ በኋላ የሚቀርብ ማንኛውም የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
- የጨረታ ሳጥኑ የጨረታ ገምጋሚ ኮሚቴና ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3:45 ታሽጎ ከጠዋቱ 4:00 በቅ/ጽ/ቤቱ የግዥ፣ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር የሥራ ሂደት ቢሮ ይከፈታል፡፡ ዕለቱ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ ይከፈታል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች ብር 60,000.00 (ስልሳ ሺህ ብር) የጨረታ ማስከበሪያ እንደተጫራቹ ምርጫ በጥሬ ገንዘብ፣ ከታወቀ ባንክ በሚሰጥ የክፍያ ማዘዣ ቼክ ወይም የባንክ ዋስትና ወይም በባንክ የተረጋገጠ ሌተር ኦፍ ክሬዲት በገቢዎች ሚኒስቴር የአዳማ ቅ/ጽ/ቤት (MINISTRY OF REVENUE ADAMA BRANCH) ስም አሰርተው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ቅ/ጽ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መበቱ የተጠበቀ ነው::
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- +251-22-21-40-10 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
በገቢዎች ሚኒስቴር የአዳማ ቅ/ጽ/ቤት
