Tender Detail

Tender Details


በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 02 ጤና ጣቢያ ለአገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 02 ጤና ጣቢያ


 

የጨረታ ማስታወቂያ

 

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 02 ጤና ጣቢያ ለአገልግሎት የሚውሉ፡-

  • ቋሚ የህክምና ዕቃዎች ግዥ
  • አላቂ የህክምና ዕቃዎች ግዥ
  • የደንብ ልብስ ግዥ
  • ልዩ ልዩ ዕቃዎች ግዥ
  • የፅዳት ዕቃዎች ግዥ
  • ቋሚ የቢሮ ዕቃዎች ግዥ
  • የፅህፈት መሳሪያዎች ግዥ
  • የኤሌክትሮኒክስ እና አይቲ ዕቃዎች ግዥ
  • የህትመት ስራዎች ግዥ
  • የተለያዩ ጥገናዎችን

በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች ለአንድ ሎት የማይመለስ 200 (ሁለት መቶ) ብር በተጨማሪም ቋሚ የህክምና እቃ ጨረታ ላይ የምትወዳደሩ ተጫራቾች ከጤና ፅ/ቤት የተሰጠውን ስፔስፊኬሽን መውሰድ ያለባችሁ መሆኑን እያሳወቅን ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት የሚቆይ ሲሆን ከ2፡30-11፡ 15 የጨረታ ሰነድ ገዝታችሁ መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

  1. ተጫራቾች በጨረታ ለመካፈል በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ምዝገባና ንግድ ስራ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን አለባቸው፡፡
  2. ቫት ተመዝጋቢና በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋገጥ የተጫራቾች የምስክር ወረቀት ያላቸው መሆን አለባቸው፡፡
  3. ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ናሙና ገቢ ማድረግ አለባቸው፤ ናሙና ያላቀረቡ ተጫራቾች ከጨረታ ውጭ ይሆናሉ፡፡
  4. የግብር ከፋይነት ቲን ሰርተፊኬት መቅረብ አለበት፡፡
  5. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን በጥንቃቄ በታሸገ ኤንቨሎፕ ኦርጅናል እና ፎቶ ኮፒ በመለየት የሚወዳደርበትን የሎት አይነት በፖስታ ላይ መግለፅ አለበት፡፡

በተጨማሪም ቋሚ የህክምና ዕቃዎችን የምትወዳደሩ ተጫራቾች የፋይናንሻልና የቴክኒክ መግለጫዎችን በተለያዩ ፖስታ ውስጥ ማስገባት አለባችሁ፡፡

የሚወዳደርበትን ሎት በግልፅ በፖስታው ጀርባ ላይ ያልገለፀ ተጫራች አይስተናገድም (ውድቅ ይደረጋል)።

ጨረታው በ11ኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በ4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በለሚ ኩራ ከ/ከተማ ወረዳ 02 ጤና ጣቢያ በኮሚቴዎች ይከፈታል፡፡

ማሳሰቢያ:- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለእያንዳንዱ ሎት ብር 5.000.00 (አምስት ሺ) በባንክ የክፍያ ማዘዣ ሰነድ (CPO) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ እንዲሁም በደብዳቤ የምትወዳደሩ ተጫራቾች ህጋዊ ደብዳቤ በማስያዝ መግዛት የምትችሉ መሆኑን ከወዲሁ እናሳውቃለን፡፡

  • ተጫራቾች በሚያቀርቡት ዋጋ ላይ ቫትን ያካተተ መሆን አለበት፡፡
  • እያንዳንዱ ሰነድ ላይ የተጫራቾች ፊርማና የድርጅታችሁ ማህተም መኖር አለበት፡፡
  • መ/ቤታችን አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  • እያንዳንዱ ሰነድ እንደ አስፈላጊነቱ 20% ሊቀንስ ወይም ሊጨምር ይችላል፡፡

አድራሻ ፦ ለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 02 ጤና ጣቢያ ከአያት አደባባይ ወደ ለገጣፎ በሚወስደው መንገድ አያት ቁጥር ፡ ኮንዶሚኒየም ፊት ለፊት 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 401

    ስልክ ቁጥር ፦ 011-8690779 / 011-8681387/

 

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 02 ጤና ጣቢያ

 

Save Tender