በመከላከያ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን የሞተር ቬይክልስ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ISUZU | FSR 4X4 OFF ROD CHASSIS TRUCK ብዛት በቁጥር 14 (አስራ አራት) በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል::
በመከላከያ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን የሞተር ቬይክልስ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ
የግልፅ ጨረታ ጥሪ ማስታወቂያ ቁጥር ሞቬኢኢ/ግጨሰ/03/2017
- በመከላከያ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን የሞተር ቬይክልስ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ISUZU | FSR 4X4 OFF ROD CHASSIS TRUCK ብዛት በቁጥር 14 (አስራ አራት) በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል::
- ተጫራቾች ከዚህ በታች የተመለከቱትን ነጥቦች በሟሟላት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ፡፡
- ማንኛውም ተጫራች አግባብነት ያለው በ2017 ዓ.ም የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና የወቅቱን ግብር የከፈሉ መሆን አለበት፡፡
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይ (VAT) የተመዘገቡና (Tin No.) ያላቸው መሆን አለበት፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡትን የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን በማያሻማ ሁኔታ መግለፅና ሙሉ አድራሻቸውን መጥቀስ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ከዋናው ሰነድ ጋር በተያያዘው የዋጋ ማቅቢያ ሰንጠረዥ መሰረት በጥራትና በተቀመጠው ስፔስፊኬሽን መሠረት ሞልተው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች በሎቱ ለቀረቡት ዕቃዎች ላይ ለመወዳደር በዘርፉ ስራወይም ንግድ ላይ ስለመሰማራታቸው ህጋዊ ማስረጃ ማቅረብ ያለባቸው ሲሆን ከዚህ ውጪ ተወዳድረው ቢገኙ ያስገቡት መወዳደሪያና ዋጋ ተቀባይነት አይኖረውም
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የመጫረቻውን ጠቅላላ ዋጋ 2% (CPO) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፤ 2% (CPO) ያላስያዘ ተጫራች ከጨረታው ውጪ ይደረጋል፡፡
- በጨረታው ተሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች 2% የጨረታ ማስከበርያ (CPO) ዋስትና የጨረታ አሸናፊው እንደታወቀ ተመላሽ ይደረግላቸዋል፡፡
- የጨረታውን አካሄድ ለማዛባት የሚሞክሩ ተጫራቾች ከጨረታው ውጪ ይሆናሉ፤ ለወደፊትም በኢንዱስትሪው ጨረታ አይሳተፉም ያስያዙትም የጨረታ ማስከበሪያ ይወረሳል፡፡
- በጨረታው አሸናፊ የሆኑ ተጫራች ከኢንዱስትሪው ጋር የሥራ አፈፃፀም ውል መፈራረም አለበት ውል ካልፈረመ የስያዘው 2% (CPO) ተወርሶ ለኢንዱስትሪው ገቢ ይደረጋል፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ በግልፅ በኢትዮጵያ ብር ነጠላ ዋጋና ጠቅላላ ዋጋ በዝርዝር መስፈር አለባቸው፡፡ በዋጋው ላይ ማንኛውም ታክስና ተጨማሪ እሴት ታክስ ያካተተ መሆኑና አለመሆኑ መግለፅ ያለበት ሲሆን ምንም ካልተባለ ዋጋው ከነቫቱ እንደሆነ ተደርጎ ይወሰዳል፡፡
- በነጠላ ዋጋና በጠቅላላ ዋጋ መካከል ልዩነት ቢኖር ነጠላ ዋጋ ተቀባይነት እንዲኖረው ተደርጎ በነጠላ ዋጋው ተመስርቶ ጠቅላላ ዋጋው ይታረማል፡፡
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን በኢንዱስትሪው ቅጥር ግቢ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፤ የጨረታ ሳጥኑ ከሚዘጋበት ሰዓት በኋላ የሚቀርብ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
- ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያቸውን በሁለት ቅጅዎች ማቅረብ አለባቸው አንደኛው ቅጅ ላይ “ዋና” በሁለተኛው ቅጅ ላይ “ኮፒ” የሚል ምልክት ማድረግ ይኖርባቸዋል፡፡ በሁለቱ መካከል ያለመጣጣም - ቢፈጠር “ዋና” ተብሎ ምልክት የተደረገበት ተቀባይነት ይኖረዋል፡፡
- ማንኛውም ተጫራቾች በሚቀርቡት የጨረታ ሰነድ ላይ የተጫራቹ ወይም የሕጋዊ ወኪሉ ስም ፊርማና የድርጅቱ ማህተም መስፈር አለበት፡፡
- በሌላ ተጫራች ላይ ተመስርቶ ዋጋ መስጠት አይቻልም፡፡
- ከዚህ በላይ በቀረበው ዝርዝር መሠረት በግንባር ቀርበው ዝርዝር መረጃ የያዘ የተጫራቾች መመሪያ እና የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል ሰነዱን መግዛት አለባቸው፡፡
- ጨረታው ለተወዳዳሪዎች ክፍት ሆኖ የሚቆይበት ጊዜ የግልፅ ጨረታ ጥሪ ማስታወቂያው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት የመጀመሪያ ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 (አምስት) የመንግስት የስራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት እስከ 11፡00 ሰዓት የስራ መውጫ ባሉት ሰአቶች ሲሆን ጨረታው በ16ኛው (በአስራ ስድስተኛው) ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዚያኑ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓትየጨረታ ሰነዱን በገዙበት ተቋም በሚገኘው መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡ እንዲሁም ተጫራቾች በራሳቸው ምርጫ ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ሳይገኙ ቢቀሩ የጨረታውን መከፈት አያስተጓጉልም፣
- ኢንዱስትሪው ያወጣውን ጨረታ ሰነድ ሳይገዛ የተወዳደረ ማንኛውም ተጫራች ከተገኘ ከውድድሩ ውጪ ይደረጋል፡፡
- አሸናፊ ተጫራቾች ውል ሲፈራረሙ የውል ማስከበሪያ ያሸነፉበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% (አስር በመቶ) ዋስትና (Perfomance Bond) ወይም የባንክ በተረጋገጠ ክፍያ ማዘዣ (CPO) ማቅረብ ይኖርባቸዋል እንዲሁም ውል ከተፈራረሙ በኃላ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ወዲያውኑ ይለቀቅላቸዋል፤
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዱን በመከላከያ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን በሞተር ቬይክልስ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ቢሾፍቱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ ስልክ ቁጥር (09 94 52 15 56 /09 36 65 65 77) ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፣
- ኢንዱስትሪው ጨረታውን የተሻለ መንገድ ካገኘ ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፤
በመከላከያ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስሪ ኮርፖሬሽን የሞተር ቬይክልስ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ቢሾፍቱ
