የሀዋሳ ከተማ አስ/ፋ/ኢ/ል/መምሪያ የሞተር ሳይክል ማቆሚያ ሼድ ግንባታ በጨረታ አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል
የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ኢኮ/ል/መምሪያ
የጨረታ ማስታወቂያ
የሀዋሳ ከተማ አስ/ፋ/ኢ/ል/መምሪያ በሀዋሳ ከተማ አስ/ከንቲባ ጽ/ቤትለሚያሰራው የሞተር ሳይክል ማቆሚያ ሼድ ግንባታ በ2017 በጀት ዓመትዕቅድ መሠረት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማስራት ያስፈለገ በመሆኑበተዘጋጀው ዲዛይን ተጠቅሞ በዘርፉ ፈቃድ ካለው ድርጅት መካከልበጨረታ አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል፡፡
በዚህ መሠረት:
ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅት መወዳደርይችላሉ፡-
- በኮንስትራክሽን ዘርፍ ደረጃ BC-6/Gc-6 እና ከዚያ በላይ ፍቃድያላቸው
- በሥራ መስኩ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ፤ የንግድ ምዝገባ ምስክርወረቀት ማቅረብ የሚችሉና የዘመኑን ግብር መክፈላቸውንየሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ ፤
- ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ ፣
- የአቅራቢነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው ፣
- የጨረታ ሰነዱን ከሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይ/ኢኮ/ልማት መምሪያቢሮ ( አዲሱ ከተማ አስተዳደር ህንፃ ) አንደኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 54 ( ሃምሳ አራት) በመቅረብ ይህ ጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀንጀምሮ ለ21 ለሃያ አንድ/ ተከታታይ ቀናት ውስጥ ቀርባችሁ ስነድ ብር500 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል ወስዶ ዋጋ ሞልቶ ማቅረብይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 100,000 (አንድ መቶ ሺህ ብር ) በባንክ የተረጋገጠ (የተመሰከረ) ሲ ፒ ኦ (CPO) ወይም ቢድ ቦንድከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ አለበት።
- ጨረታ ሰነዱ በሰም ለየብቻቸው በታሸገ ኤንቬሎፕ አንድ ኦሪጂናልእና ሁለት ኮፒ (ቴክኒካል እናፋይናንሻል) በመያዝ ይህ ማስታወቂያከወጣበት ቀን ጀምሮ 21 (ሃያ አንድ) ተከታታይ ቀናት በፋይ/ኢኮ/ልማ/ መምሪያ ቢሮ ቁጥር 54 (ግዢ ኬዝ ቲም ) ለዚሁ ጨረታበተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው በ22ኛው ቀን ከቀኑ 3፡00 ሰዓት ታሽጎ ተጫራቾችወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበትም ሆነ ባልተገኙበት ከቀኑ3፡30 ሰዓት በቢሮ ቁጥር 54 ይከፈታል፡፡ ይህ ቀን በበዓላት ቅዳሜወይም እሁድ ከሆነ ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀን በተመሣሣይ ሠዓትየሚታሽግና የሚከፈትበት ቀን ይሆናል፡፡ የበዓል ቀን ከሆነ ደግሞበሚቀጥለው የሥራ ቀን ጨረታው ይከፈታል ፡
- ማንኛውም ተጫራች በሲዳማ ክልል እና ሀዋሳ ከተማ አስተዳደርውስጥ ተመሳሳይ ሥራ በእጁ ላይ ካለና የሥራው አፈጻጸም 70% ካልደረሰ በጨረታ መወዳደር አይችልም፡፡ ሥራው 70% እና በላይየደረሰ ከሆነ ከሚመለከተው የመንግስት አካል ማረጋገጫ ደብዳቤማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
- በጨረታ አከፋፈት ስነ-ስርዓት የተነበበው ዋጋ እና በአርትሜቲክቼክ በሚደረግበት ግዜ በሁለቱ መካከል ከ2% (ከሁለት ፐርሰንት) በላይ ሆነ በታች ልዩነት ካለ ተጫራቹ በቀጥታ ከጨረታ ውጪይደረጋል፡፡
- ለጨረታ ያስገቡት ዋጋ ከቀረበ የመሐንዲስ ዋጋ ጥናት ጋር ሲነፃፀርወደ ላይ ከአሥራ አምስት ፐርሠንት (15%) በላይ ከሆነ በቀጥታከጨረታ ውጪ ይደረጋል፡፡
- ለጨረታ ያስገቡት ዋጋ ከቀረበ የመሐንዲስ ዋጋ ጥናት ጋር ሲነፃፀርወደ ታች ከአሥራ አምስት ፐርሠንት (15%) በታች ከሆነ ለእንዳንዱሥራ ዝርዝር ተጨባጭ የወቅቱ ገበያ የዋጋ ትንተና (Direct Unite cost Analysis sheet) ማቅረብ የሚችል እና ለዚህም መ/ቤቱየጠየቀውን የውል ማስከበሪያ ዋስትና ገንዘብ ወይም መያዣገንዘብ መጠን ማቅረብ የሚችል መሆን ይኖርበታል፡፡
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ስልክ ቁጥር 046-220-0963/046-212-1334
የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና/ኢኮ/ል/መም/ያ
ሀዋሳ
