በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን የሚገኙ የሃራጉ፤ የጨፈ ቡሉቅ እና የቱሉ ላፍቶ የገ/ህ/ ስራ ዩኒዬኖች ለ2017/2018 ዓ.ም የምርት ዘመን የሚውል የተለያዬ የአፈር ማዳበሪያዎችን ከሻምቡ እና ከኮምቦልቻ ከተሞች ወደ ዞን ውስጥ ለሚገኙ መሠረታዊ የገ/ህ/ሥራ ማህበራት ለማጓጓዝ የጭነት ማመላለሻ ባለንብረቶች በጨረታ አወዳድሮ ማስጫን ይፈልጋል።
በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን የሃራጉ የገበሬዎች ህብረት ሥራ ዩኒዬን ኃ/የተዳ/ ማህበራት
በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን የሚገኙ የሃራጉ፤ የጨፈ ቡሉቅ እና የቱሉ ላፍቶ የገ/ህ/ ስራ ዩኒዬኖች ለ2017/2018 ዓ.ም የምርት ዘመን የሚውል የተለያዬ የአፈር ማዳበሪያዎችን ከሻምቡ እና ከኮምቦልቻ ከተሞች ወደ ዞን ውስጥ ለሚገኙ መሠረታዊ የገ/ህ/ሥራ ማህበራት ለማጓጓዝ የጭነት ማመላለሻ ባለንብረቶች በጨረታ አወዳድሮ ማስጫን ይፈልጋል።
በአጠቃላይ 411,170 /አራት መቶ አሥራ አንድ ሺ አንድ መቶ ሰባ/ ኩንታል ሲሆን በጨረታው ላይ ለመሳተፍ የምትፈልጉ።
መስፈረቶች
- በጨረታው ላይ ለመሳተፍ ህጋዊ የትራንስፖርት ፍቃድ ያለው፤ የዘመኑን 2016 ወይም 2017 ዓ/ም ግብር የከፈለና 1000 ኩንታል በአንዴ የመጫን አቅም እንዳለው ከሚመለከተው የትራንስፖርት ባለስልጣን የብቃት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችል።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ /CPO/ ከጠቅላላ ዋጋ 2% በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማስያዝ የሚችል፡፡ አንደዚሁም ሲፒኦ ካሰራበት ባንክ የማረጋገጫ ደብዳቤ ገንዘብ መኖሩን የሚገልጽ ዋናውን ማቅረብ አለበት።
- ተጫራቾች በጨረታው ሰነድ ዝርዝር በመስራት የሚጓጓዝበትን ዋጋ ለአንድ ኩንታል በኪሎ ሜትር ወይም የአንድ ኩንታል ማጓጓዣ ከመነሻ እስከ መድረሻ በብር ሞልተው በማሸግ ከዋጋ ማቅረብያቸው ጋር አያይዘው በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ኦርጅናልና ኮፒ በተለያዩ ኤንቨሎፕ ማቅረብ አለባቸው።
- ጨረታው አየር ላይ የሚውለው ጨረታው በጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ 15 /አስራ አምስት/ ተከታታይ ቀናት ይሸጣል።
- ተጫራቾች ጨረታ ሰነዳቸው በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን የህብረት ስራ ማስፋፊያ / ኤጀንሲ በታሸገው ሳጥን ጨረታው ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለተከታታይ ቀናት ማስገባት ይቻላል። እንዲሁም ጨረታው የሚከፈተው በ15ኛው ቀን ከሰዓት 11፡00 ተዘግቶ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዞኑ ህብረት ሥራ ኤጀንሲ ቢሮ ቁጥር 1/አንድ/ ወይም በሚመቸው ክፍል ይከፈታል።
- በአንድ ማራገፊያ ቦታ ከሚቀርበው የአፈር ማዳበሪያ በታች ወይም ከፋፍሎ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም።
- በተሰጠው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት አይችልም።ውል ከገቡ በኋላ በ120 ቀናት ውስጥ አጓጉዞ የሚያጠናቅቅ መሆን አለበት።
- አሸናፊ ድርጅት ማሸነፉ በደብዳቤ ከተረጋገጠበት ቀን ጀምሮ እስከ 5/አምስት/ ተከታታይ ቀናት ውስጥ ከጠቅላላው ዋጋ 10% የመልካም ስራ አፈጻጸም ዋስትና ሲፒኦ በማቅረብ ከዩኒዬኑ ጋር ውል መፈራረም አለበት።
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ በመጀመሪያ ጨረታ ላይ የተሳተፉት ብር 1500 (አንድ ሺ አምስት መቶ ብር)፣ እንደዚሁም አዲስ ተጫራቾች ደግሞ ብር 3000 /ሶስት ሺ ብር/ የማይመለስ ከፍለው ከኮምቦልቻ፤ ከሻምቡ እና ከቱሉ ላፍቶ መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች በሚወዳደሩበት ወረዳ ውስጥ የሚገኙት መሰረታዊ ማህበራት በሙሉ ላይ የመወዳደር ግዴታ አለባቸው።
- ከዚህ በፊት /ሲ.ፒ.ኦ/ ተቀጥተው 3/ሶስት/ ዓመት ያልሞላው ድርጅት በተቀጡበት ዩኒዬን ላይ በጨረታው አይሳተፍም።
- ድርጅቱ ከተፈራረመው የአፈር ማዳበሪያ መጠን 40% በመቀነስ ወይም በመጨመር የማስጫን መብት አለው።
- ከላይ የተጠቀሱትን መስፈርቶች ሁሉንም አሟልቶ ያልተገኘ/ያላቀረበ/ ተጫራች ከጨረታ ውጭ ይሆናል።
- በአንድ ጣቢያ ላይ ተጫራቾች እኩል ዋጋ ከሰጡ ብዙ ኩንታል ለሚያጓጉዘው ቅድሚያ ይሰጣል።
- ተጫራቾች ጨረታውን ካሸነፉ በኋላ በድርጅቱ አመራር ላይ ተመሰርቶ ውል የሚዋዋል ይሆናል።
- ጨረታውን ያሸነፈ ተጫራች ክፍያ መጠን መጠየቅ የሚችለው ቦታ /ማህበር/ ህጋዊ ሰነድ ሰብስቦ ካቀረበ በኋላ ነው።
- ዩኒዬኑ መሠረታዊ ማህበር ላይ የሸነፉ ተጫራቾችን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ ወደ ሌላ መሠረታዊ ማህበር የማሳለፍ መብት አለው።
- አንድ ትራንስፖርተር ያላሻነፈ መሠረታዊ ማህበር ላይ ማዳበሪያውን ካራገፈ በሌላ ትራንስፖርተር መሠረታዊ ማህበር ላይ በአሸነፈው ዋጋ መውሰድ አለበት።
- ዩኒዬኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ እና በጨረታው ያለመገደድ መብት አለው።
ለተጨማሪ መረጃ
- ሃራጉ 0917721512/0964670223 ጨፌ ቡሉቅ 0910120067 ቱሉ ላፍቶ 0917091782 እና ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን ሕ/ሥራ ማህበራት ማስፋፊያ ጽ/ቤት/0913652830 መጠየቅ ይቻላል።
በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን የሃራጉ የገበሬዎች ህብረት ሥራ ዩኒዬን ኃ/የተዳ/ ማህበራት
