የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ በዘርፉ የተሰማሩ ትራንስፖርተሮችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ የሎቤድ ትራንስፖርት አገልግሎት ግዥ መፈጸም ይፈልጋል።
Ethiopian Sugar Industry Group (የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ)
ብሔራዊ ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር LP/OT/26/S|G/2017
- የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ በዘርፉ የተሰማሩ ትራንስፖርተሮችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ የሎቤድ ትራንስፖርት አገልግሎት ግዥ መፈጸም ይፈልጋል።
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ብቁ ተጫራቾች ህጋዊ ለ2017 ዓ.ም የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን የሚያረጋግጥ በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል ከግብር ሰብሳቢው ባለሥልጣን የተሰጠ የታክስ ክሊራንስ፣ በጨረታለመሳተፍ የሚያስችል የምስክር ወረቀት የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (Tin No.) ሠርተፍኬት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት ምዝገባ የምስክር ወረቀት እና የመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ወይም ሌላ የሚመለከተው የመንግስት አካል ባዘጋጀው የዕቃ አቅራቢዎች አገልግሎት ሰጪ ዝርዝር ውስጥ መመዝገባቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው።
- ብቁ ተጫራቾች በአማርኛ ቋንቋ የተዘጋጀውን የተሟላ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 300.00 (ብር ሶስት መቶ) በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ወደ ግሩፑ ሂሳብ ቁጥር 1000000888862 በማስገባትና ደረሰኙን በማቅረብ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጨረታው መክፈቻ ቀን ድረስ ዘወትር በሥራ ሰዓት (ከሰኞ እስከ ዓርብ፣ ከሰዓት በፊት ከ2፡00-6፡00 እና ከሰዓት በኋላ ከ7፡00-11፡00) ቀጥሎ ከተመለከተው አድራሻ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።
የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ
ግዥና ንብረት አስተዳደር መምሪያ
አድራሻ አዲስ አበባ ልደታ ክ/ከተማ
ጨለለቅ አልሳም ህንጻ ፊት ለፊት
ፊሊፒስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 220
ስልክ ቁጥር +251 11 551 6271 ወይም 11-550-0417፣
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን በኤንቨሎፕ በማሸግ ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል. ጨረታው በጨረታው መክፈቻ ላይ መገኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በተራ ቁጥር 3 በተገለፀው አድራሻ መጋቢት 5 ቀን 2017 ዓ.ም. ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ይከፈታል። ዘግይቶ የሚቀርብ የመጫረቻ ሰነድ ተቀባይነት የለውም።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ ብር) በባንክ የተመሠከረለት የክፍያ ማዘዣ (CPO) ከቴክኒክ መጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
- የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትናው ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለዘጠና (90) ቀናት ፀንቶ የሚቆይ መሆን ይኖርበታል።
- የጨረታ ዋጋ ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለስልሳ (60) ቀናት ይሆናል።
- ግሩፑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው
የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ
