በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ለዋና መ/ቤት አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ሎት1. ዴስክቶፕ ኮምፒዩተሮች፣ ላፕ ቶፕ ኮምፒዩተሮች፣ ፕሪንተሮች እና ፎቶ ኮፒ ማሽኖችን ሎት2. የስቴሽነሪ ዕቃዎችን እና ሎት3. ቪዲዮ ካሜራን (video camera) በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
Chemical Industry Corporation (ኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን)
በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ለዋና መ/ቤት አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ሎት1. ዴስክቶፕ ኮምፒዩተሮች፣ ላፕ ቶፕ ኮምፒዩተሮች፣ ፕሪንተሮች እና ፎቶ ኮፒ ማሽኖችን ሎት2. የስቴሽነሪ ዕቃዎችን እና ሎት3. ቪዲዮ ካሜራን (video camera) በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ማንኛውም ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩ መስፈርቶችን አሟልተው መወዳደር ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉበት ማስረጃ (tax clearance)፣ የግብር ከፋይ የምስከር ወረቀት፣ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስራ አምስት (15) ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ ይውላል፡፡ ስለሆነም ተጫራቾች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአየር ላይከዋለበት ዕለት ጀምሮ ያዘጋጁትን የጨረታ ሠነድ ዘወትር ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 2፡00 እስከ 6፡30 እና ከሰዓት በኋላ ከ7፡00 እስከ 11፡00 የማይመለስ ብር አንድ መቶ አምሳ ብር (150.00) በመክፈል ቦሌ አካባቢ ፍሬንድ ሺፕ ህንፃ ጀርባ 200 ሜትር ገባ ብሎ በሚገኘው በኮርፖሬሽኑ ዋና መ/ቤት አምስተኛ ፎቅ የኦፕሬሽን መምሪያ ቢሮ ቁጥር 05 እየቀረቡ የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ላይ የጨረታ ሳጥኑ የሚዘጋ ይሆናል፡፡ የጨረታ ሳጥኑ ከተዘጋ በኋላ የሚቀርብ የጨረታ መወዳደሪያ ሠነድ ተቀባይነት የለውም፡፡ 16ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይዘጋል።
- ጨረታው በተዘጋበት ዕለት ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን መሰብሰቢያ አዳራሽ ውስጥ የሚከፈት ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ኦሪጅናል እና ኮፒ ለይተው በተለያየ ኤንቨሎፕ በጥንቃቄ በማሸግ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ስም ለጨረታ ያቀረቡትን ዋጋ ሁለት በመቶ (2%) በባንክ ሲፒኦ ወይም በቅድመ ሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ከቴክኒክ ኦሪጅናል ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ኮርፖሬሽኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ ስቁ 011-6-62-90-15/011-6-15-14-68
የኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን
