የአማራ ብሄራዊ ከልላዊ መንግስት የሰሜን ሸዋ ዞን የሞጃና ወደራ ወረዳ የሰላድንጋይ ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት በከተማው ውስጥ ለሚሰራ መንገድ ስራ የሚሆን ግሪደር ፣ ሮሎ ፣ ሎደር ገልባጭ እና የመንገድ መብራት በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ማወዳደር ይፈልጋል።
የሰሜን ሽዋ ዞን የሞጃና ወደራ ወረዳ የሰላድንጋይ ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት
ብሔራዊ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የአማራ ብሄራዊ ከልላዊ መንግስት የሰሜን ሸዋ ዞን የሞጃና ወደራ ወረዳ የሰላድንጋይ ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት በከተማው ውስጥ ለሚሰራ መንገድ ስራ የሚሆን ግሪደር ፣ ሮሎ ፣ ሎደር ገልባጭ እና የመንገድ መብራት በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ማወዳደር ይፈልጋል።
ስለዚህ ተወዳዳሪዎች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል።
- በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
- የግብር መለያ ቁጥር /Tin no/ ያላቸው
- የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1 - 4 የተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የማሽኖችን ዝርዝር መገለጫ /ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ሲገዙ የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ እና የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና/ ቢድ ቦንድ ለሚወዳደሩበት ብር ወይም የዕቃውን ጠቅላላ ዋጋ 1% በባንክ የተረጋገጠ የከፍያ ትዕዛዝ (ሲ.ፒ.ኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንከ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በሞ/ወ/ወ/የሰላድንጋይ ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ማሰታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀን ማስገባት ይኖርባቸዋል። ጨረታው በወጣበት በ15 ኛው ቀን 11፡30 ይዘጋል።
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ወይም ባልተገኙበት በሞ/ወ/ወ/በሰላድንጋይ ከተማ መሪ ማ/ቤት በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ይከፈታል።
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ተጫራቹ ከላይ የተዘረዘሩትን ሁሉንም የማሽን አይነቶች በአንድ ላይ የሚያቀርብ መሆን አለበት፡፡
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 7 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም ስልክ ቁጥር 0116250497 /0921127777/ በመደወል ማግኘት ይቻላል፡፡ ይህ ማስታወቂያ የሚከፈትበት ቀን ቅዳሜ፣ እሁድና በበዓላት ቀን የሚውል ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን የሚከፈት መሆኑን እንገልፃለን፡፡
በአብክመ የሰሜን ሸዋ ዞን የሞጃና ወደራ ወረዳ
የሰላድንጋይ ከተማ መሪ ማ/ቤት
