Tender Detail

Tender Details

  • Company Kombolcha Customs Branch (የኮምቦልቻ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት)
  • Address Ethiopia Kombolcha City, Kembolcha, Ethiopia, Phone: 0116730520
  • Website
  • Deadline11 Mar 2025, 10:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Office Machines And Computers

በኢፌዲሪ ጉምሩክ ኮሚሽን ኮምቦልቻ ቅ/ጽ/ቤት ከዚህ በታች የተገለጹትን እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል።

Kombolcha Customs Branch (የኮምቦልቻ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት)


 

ብሄራዊ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር ኮ/ቻ ጉም 05/2017

 

በኢፌዲሪ ጉምሩክ ኮሚሽን ኮምቦልቻ ቅ/ጽ/ቤት ከዚህ በታች የተገለጹትን ማለትም፣

  1. የሰራተኞች የስራ ልብስ (ፖሊስተር ጨርቅ፣ የሰነድ መያዣ ቦርሳና ሌሎች)
  2. ልዩ ልዩ አላቂ የቢሮ ዕቃዎች (የፕሪንተር ወረቀት A4 size፣ የቃለ ጉባኤ መዝገብና ሌሎች)
  3. የጀነሬተር ዘይት፣ ቅባትና መለዋወጫዎች (ራዲያተር ኩላንት፣ የዘይት ፊልተርና ሌሎች)
  4. ልዩ ልዩ የጽዳት ዕቃዎች (ዲቶል፣ መወልወያ ዘሃ የውጪ፣ ላርጎ፣ በረኪና እና ሌሎች)
  5. ሌሎች ቋሚ አላቂ ዕቃዎች (ካልኩሌተር፣ ሌዘር የላፕቶፕ ቦርሳ፣ የፕሮጀክተር ፖርሳና ሌሎች)
  6. የተሽከርካሪ መለዋወጫዎችና ጎማዎች (Tube Tyre፣ ፍሬንቻ፣ አሞርዝራተርና ሌሎች)
  7. የቤት ጥገና ቁሳቁስ እቃዎች (የኮንስትራክሽን እቃዎች (Drill Machine፣ Breaker እና ሌሎች)
  8. ቋሚ ዕቃዎች (ኮምፒውተርና ተዛማች (ዴስክቶፕ ኮምፒውተር፣ ሰርቨር ፕሪንተርና ሌሎች)
  9. የህክምና ዕቃዎች እና መገልገያዎች Autoclave/hot air oven Pulse Oximeter እና ሌሎች)
  10. የሆቴል መስተንግዶ አገልግሎት ግዥ በሎት በደሴ ከተማ ብቻ በብሄራዊ ግልጽ ጨረታ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል።

ስለሆነም ከዚህ በታች የተገለፁትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች ቀርበው መወዳደር ይችላሉ።

  1. በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን የሚገልፅ የታደሰ ታክስ ክሊራንስ፣የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሠርቲፊኬት፣ ከመንግስት ግዥ አገልግሎት የአቅራቢነት ፕሪንት የተደረገ ማስረጃ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  2. ተጫራቾች የሚያስይዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትናን በተመለከተ፡-

ለስራ ልብስ ብር 40,000.00 (አርባ ሺህ ብር)

ለአላቂ ዕቃዎች ብር 30,000.00 (ሰላሳ ሺህ ብር)

ለጀነሬተር ዘይት፣ ቅባትና መለዋወጫዎች ብር 25,000.00 (ሃያ አምስት ሺህ ብር)

ለጽዳት ዕቃዎች ብር 25,000.00 (ሃያ አምስት ሺህ ብር)

ለቋሚ አላቂ ዕቃዎች ብር 20,000.00

ለተሽከርካሪ መለዋወጫዎችና ጎማዎች ብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር)

ለኮንስትራክሽን እቃዎች ብር 20,000.00 (ሃያ ሺህ ብር)

ቋሚ ዕቃዎች ብር 60,000.00 (ስልሳ ሺህ ብር)

ለህክምና ዕቃዎች እና መገልገያዎች ብር 5,000.00 (አምስት ሺህ ብር እና መስተንግዶ አገልግሎት ግዥ በሎት ብር 30,000.00 (ሰላሳ ሺህ ብር) በባንክ የክፍያ ማዘዣ (CPO) ወይም በቢድ ቦንድ ማስያዝ አለባቸው።

  1. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን የካቲት 17/2017 ዓ.ም ጀምሮ እስከ መጋቢት 01/2017 ዓ.ም ከቀኑ 11፡00 ድረስ በሥራ ቀናት ውስጥ ብቻ በኮምቦልቻ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት 2ኛ ፎቅ ሀብት አስተዳደር የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 205 ድረስ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።
  2. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በጨረታ ሰነዱ ላይ በጥንቃቄ በመሙላት በእያንዳንዱ ገጽ ፊርማና የድርጅቱን ማህተም በመምታት ዋናውንና ኮፒውን በፖስታ ውስጥ አስገብቶ በማሸግ በቅ/ጽ/ቤታችን ስም የጨረታ መለያ ቁጥሩንና የግዥውን ዓይነት በመግለጽ በኤንቨሎፕ ላይ በመፃፍ ለዚህ ተግባር በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
  3. የሆቴል መስተንግዶ አገልግሎት ግዥን በሎት በተመለከተ:- ተጫራቾች ቅድመ ግዥ መስፈርቶችንና ቴክኒካል ዶክመንቶችን በአንድ ኤንቨሎፕ ፋይናንሻል ዶክመንቶችን በሌላ ኤንቨሎፕ በማድረግና ፖስታው ላይ በመጻፍ ለዚህ ተግባር በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ አለባቸው።
  4. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ መጋቢት 02/2017 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡00 ድረስ የዕቃዎቹን ዋጋ ሞልተው ከአስፈላጊ ሰነዶች ጋር በኮምቦልቻ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት 2ኛ ፎቅ ሀብት አስተዳደር የስራ ሂደት ቢሮ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ብቻ ማስገባት አለባቸው።
  5. ጨረታው መጋቢት 02/2017 ዓ.ም ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዚሁ ዕለት 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኮምቦልቻ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት 2ኛ ፎቅ ሀብት አስተዳደር የስራ ሂደት ቢሮ ይከፈታል።
  6. ጨረታው ከተከፈተ በኋላ የቀረበውን የጨረታ ሰነድ መቀየር፣ ማሻሻል ወይም ከጨረታ ራስን ማግለል አይቻልም፡፡
  7. የተሰረዘ፣ የተደለዘ፣ የተፋፋቀ ወይም በግልጽ የማይነበብ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረው።
  8. የጨረታ አሸናፊዎች ዕቃዎቹን አገልግሎቱን እስከ ኮምቦልቻ ቅ/ጽ/ቤት ድረስ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
  9. መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  10. ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 033 551 1487 በመደወል መጠየቅ ይቻላል።

 

በኢፌዲሪ ጉምሩክ ኮሚሽን ኮምቦልቻ ቅ/ጽ/ቤት

 

Save Tender