Tender Detail

Tender Details

  • Company የአዳማ ጉምሩክ ኮሚሽን ቅርንጫፍ ጽ/ቤት
  • Address አዳማ በከልቻ ትራንስፖርት አክሲዮን ማህበር አጠገብ ያለው ቢሮአችን ሦስተኛ (3) ፎቅ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 022-211-58-07
  • Website
  • Deadline03 Mar 2025, 10:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Vehicle

በአዳማ ጉምሩክ ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት በህግ መተላለፍ ምከንያት በመጋዘናችን ተወርሰው የሚገኙ 4 ተሽከርካሪዎችን በግልፅ ጨረታ ባለበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

የአዳማ ጉምሩክ ኮሚሽን ቅርንጫፍ ጽ/ቤት


 

ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 27/2017

 

በአዳማ ጉምሩክ ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት በህግ መተላለፍ ምከንያት በመጋዘናችን ተወርሰው የሚገኙ 4 ተሽከርካሪዎችን በግልፅ ጨረታ ባለበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ በዚህም መሰረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የጨረታ መስፈርቶች የሚያሟላ ግለሰብም ሆነ ድርጅት በጨረታው መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እየገለፅን፡-

  1. የግልፅ ጨረታ ሰነዱን የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ዘወትር ከሰኞ እስከ አርብ ሙሉ ቀን በስራ ሰዓት እና ቅዳሜ ጠዋት ከ2፡00-6፡00 ሰዓት በአዳማ ከተማ በከልቻ ትራንስፖርት አ.ማ ግቢ ውስጥ በሚገኘው ቅ/ጽ/ቤቱ የገቢ ሂሳብ ዋስትናዎች አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 11 የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በመግዛት በጨረታ የወጠቱን ተሽከርካሪዎችን ማየት የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
  2. ማንኛውም ተጫራች ለሚወዳደርባቸው ተሽከርካሪዎች ለመግዛት የሚያቀርበውን የመጫረቻ ዋጋ አምስት በመቶ (5%) ለጨረታው ማስከበሪያ ዋስትና የሚሆን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ በባንክ በተመሰከረለት (CPO) CUSTOMS COMMISSION ADAMA BRANCH OFFICE በሚል የጨረታው ሳጥን ከመዘጋቱ በፊት በጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  3. በጨረታው ላይ የቀረቡት ተሸከርካሪዎች ከአስመጭው ወይም ባለቤትና ቤተሰብ ከሆነ ሰው በስተቀር ማንኛውም ዕድሜው ከ18 ዓመት በላይ የሆነ ኢትዮጵያዊ ቅድመ ሁኔታዎች ማሟላት ሳያስፈልገው የታደሰ መታወቂያ በመያዝ በጨረታው ሊሳተፉ ይችላሉ።
  4. በጨረታው ለቀረቡ ተሽከርካሪዎች የተቀመጠ የመነሻ ዋጋ የተጨማሪ እሴት ታከክስ /ቫት/ ያካተተ በመሆኑ ተጫራቾች የሚሰጡት የማሸነፊያ ዋጋ የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ጨምረው መሆን አለበት።
  5. በጨረታ ለመሸጥ የወጡ ተሽከርካሪዎች በአዳማ ከተማ በከልቻ ትራንስፖርት አ.ማ ግቢ መጋዘን 10 (ሜዳ ላይ) ስለሚገኙ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 7 ተከታታይ ቀናት አየር ላይ ከዋለ በኋላ ሳጥኑ በስምተኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ታሽጎ 4፡15 ሰዓት የሚከፈት ሲሆን ነገር ግን ስምንተኛው ቀን በዓል ወይም እሁድ ቀን የሚውል ከሆነ ጨረታው የሚካሄደው በተመሳሳይ ሰዓት በሚቀጥለው የስራ ቀን ይሆናል።
  6. የግልጽ ጨረታ ሳጥኑ የሚከፈትበት ቦታ የጨረታ ሳጥኑ በሚገኝበት የቅ/ጽ/ቤቱ የውርስ መጋዘን አስተዳደር የስራ ሂደት ቢሮ በአዳማ ከተማ በሬቻ አካባቢ መ/ቤቱ አዲስ በተከራየው ቢሮ ግቢ ውስጥ ሲሆን ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ይከፈታል፡፡ሆኖም ተጫራቾች ካልቀረቡ ታዛቢዎች ባሉበት የጨረታው ሳጥን ይከፈታል።
  7. አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸውን በማስታወቂያ ከተገለፀላቸው ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ ተሽከርካሪውን መረከብ ይኖርባቸዋል፡፡
  8. ከላይ በተ/ቁ 7 ላይ በተገለፁት ቀናት ውስጥ ክፍያውን ገቢ ያላደረገ እና ንብረቱን ያልወሰዱ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት (CPO) ለመ/ቤቱ ገቢ ሆኖ ተሽከርካሪዎች በድጋሚ ለጨረታ ይቀርባሉ፡፡
  9. ለጨረታ የቀረቡት ተሸከርካሪዎች ሽያጫቸውን የሚፈፀመው ባሉበት ሁኔታ ስለሆነ ተጫራቾች ሌላ ተመሳሳይ ወይም ተጨማሪ ዕቃ መጠየቅ አይችሉም።
  10. ከኦርጅናል የጨረታ ሰነድ ውጭ በሌላ ሰነድ ተሞልቶ የሚቀርብ ዋጋ በት/ጽ/ቤቱ ተቀባይነት የለውም፡፡
  11. ከጨረታ መነሻ ዋጋ በታች ወይም እኩል መነሻ ዋጋ ሞልቶ ያቀረብ ተጫራች ከጨረታው ውድድር ይሰረዛል፡፡
  12. ተጫራቾች በእያንዳንዱ የጨረታ ሰነዶች ላይ የተጫራቾች አድራሻ በሚለው ቦታ ላይ ስማቸውን እና ሙሉ አድራሻቸውን ፊርማቸውን ድርጅት ከሆነም የድርጅታቸውን ማህተም በማድረግ አሟልተው ማቅረብ አለባቸው።
  13. በጨረታው ለሽያጭ የቀረቡት ተሽከርካሪዎች የጨረታ ሳጥኑ በሚገኝበት በአዳማ ከተማ በሬቻ አካባቢ መ/ቤቱ አዲስ በተከራየው ቢሮ ግቢ ድረስ በመሄድ በጨረታው ለመሳተፍ የሚያስፈልገውን የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተመሰከረለት CPO፣ የጨረታ ሰነዱን እና የቀበሌ መታወቂያውን ኮፒ በፖስታ በማሸግ ሳጥኑ ከመዘጋቱ በፊት ለጨረታ የተዘጋጀውን ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  14. ማንኛውም ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ በጨረታ ሰነዱ የተሰጠውን ዋጋና መግለጫ መለወጥ እና ማሻሻል አይችሉም፡፡
  15. ማንኛውም ተጫራች 100 ብር ሰነድ የገዛበትን ደረሰኝ ከአስፈላጊው መረጃዎች ጋር አያይዞ በጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ያለበት፡፡
  16. ቅ/ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

ለተጨማሪ መረጃ፡-  በስልክ ቁጥር፡- 022-2-11-89-25 ደሙሎ መጠየቅ ይቻላል

 

አዳማ ጉምሩክ ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት

 

Save Tender