አዲስ አበባ አስተዳደር በቦሌ ከፍለ ከተማ ወረዳ 14 ፋይናስ ጽ/ቤት ከዚህ በታች ለተዘረዘሩት ሎት1 የደንብ ልብስ እና የስፖርት እቃዎች ሎት 2 ኤሌክትሮኒከስ እና ቋሚ እቃዎች ሎት 3 የጽዳት እቃዎች ሎት 4 አላቂ የፅህፈት መሳሪያ ሎት 5 የህዝብ ትራንስፖርት ሎት 6 መስተንግዶ ሎት 7 ዘር ሎት8 የዲኮር እቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በአዲስ አበባ የቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 14 ፋይናስ ጽ/ቤት
ግልጽ ጨረታ ግዢ ማስታወቂያ የጨረታ መለያ ቁፕር 002/2017 ዓ.ም
አዲስ አበባ አስተዳደር በቦሌ ከፍለ ከተማ ወረዳ 14 ፋይናስ ጽ/ቤት ከዚህ በታች ለተዘረዘሩት ሎት1 የደንብ ልብስ እና የስፖርት እቃዎች ሎት 2 ኤሌክትሮኒከስ እና ቋሚ እቃዎች ሎት 3 የጽዳት እቃዎች ሎት 4 አላቂ የፅህፈት መሳሪያ ሎት 5 የህዝብ ትራንስፖርት ሎት 6 መስተንግዶ ሎት 7 ዘር ሎት8 የዲኮር እቃዎች ጨረታውን ለመሳተፍ የሚፈልጉ ሕጋዊ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ መሆን አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩበትን ሕጋዊ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር ለመክፈላቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚ/ር በአቅራቢነት የተመዘገበና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያለው፣
- የተጨማሪ እሴት ታከስ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፡፡
- ተጫራቾች ከዚህ በታች የተጠቀሰውን የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ CPO በታሸገ ኤንቬሎፕ ማቅረብ አለባቸው፡፡
ሎት ቁጥር ሎት ዝርዝር የተጠየቀው የጨረታ ማስከበሪያ በኢትዮጵያ ብር
|
ሎት |
የእቃ አይነት |
የጨረታ ማስከበሪያ ዋጋ |
|
1 |
የደንብ ልብስ እና የስፖርት እቃዎች |
5000 |
|
2 |
ኤሌክትሮኒክስ እና ቋሚ እቃዎች |
12000 |
|
3 |
የጽዳት እቃዎች |
3000 |
|
4 |
አላቂ የፅህፈት መሳሪያ |
4000 |
|
5 |
የህዝብ ትራንስፖርት |
1000 |
|
6 |
መስተንግዶ |
2000 |
|
7 |
ዘር |
800 |
|
8 |
የዲኮር እቃዎች |
5000 |
- የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በየሎቱ የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል የተዘጋጀውን ሰነድ ከተቋሙ ቢሮ ቁጥር 6 እየቀረቡ መግዛት ይችላሉ፤
- ተጫራቶች ጨረታ ከወጣበት ቀን አንስቶ ባሉት 10 (አስር) ተከታታይ የስራ ቀናት 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 6 በመምጣት ዋጋው የተሞላበትን የጨረታ ሰነዱን ዋናውንና ፎቶ ኮፒ ለየብቻው በማሸግ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው::
- ጨረታው በ10ኛው ቀን ታሽጎ በማግስቱ ከቀኑ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተሰጠው ተመሳሳይ ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች ያሸነፉበትን ዋና የውል ማስከበሪያ 10% ማስያዝ አለባቸው
- ተጫራቾች ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ለሚወዳደሩበት ናሙና ለሚቀርብባቸው ዕቃዎች ናሙና ማቅረብ አለባቸው፡፡ ናሙና የማይቀርብባቸው ቋሚ እቃዎች መስሪያ ቤቱ ባቀረበው እስፔስፊኬሽን መሰረት ማቅረብ አለባቸው::
- የጨረታ አሸናፊ ድርጅት ያሸነፈበትን እቃዎች በ5 ቀናት ውስጥ ለመስሪያ ቤቱ በራሱ ትራንስፖርት ማስረከብ ይኖርበታል፡፡
- መ/ቤቱ ለጨረታ ካቀረበው እቃ በተጨማሪ እስከ 20% የመቀነስም ሆነ የመጨመር መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
- በመጨረሻ የጨረታ የሚታሸግበትና የሚከፈትበት ቀን ዕለቱ የበዓል ቀን ከሆነ በማግስቱ 4:30 ላይ የሚከፈት ይሆናል፡፡
አድራሻ:- ቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 14 አስተዳደር ፋይናስ ጽ/ቤት ገርጅ ናይጀሬያ ኢምባሲ አፓርትመንት አጠገብ ወደ ውስጥ ገባ ብሎ ወይም ገርጂ ፖሊስ ጣቢያ ጀርባ
ለበለጠ መረጃ፡- ስልክ ቁጥር 0118721213
ማሳሰቢያ፡- በመጨረሻም የጨረታ ሳጥን የሚገኝበት ቦታ ጨረታው ከተዘጋ በኋላ የሚቀርብ ፤ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
በአዲስ አበባ የቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 14 ፋይናስ ጽ/ቤት
