አልቪማ የምግብ እምራች ኃ/የተ/የግ/ማህበር ይዞታው አዲስ የሆነ (15000 KM) የ2021 ሞዴል MXAA54LANXGB ቶዮታ RAV4 ተሽከርካሪን በሁለተኛ ዙር በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
Alvima Foods Complex PLc (አልቪማ የምግብ አምራች ኃ/የተ/የግ/ማህበር)
በድጋሚ የመጣ ሁለተኛ ዙር የተሽከርካሪ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር አ/ የም/አም/ኃ/የተ/የግ/ማህበር ሽያጭ /0006/2025
አልቪማ የምግብ እምራች ኃ/የተ/የግ/ማህበር ይዞታው አዲስ የሆነ (15000 KM) የ2021 ሞዴል MXAA54LANXGB ቶዮታ RAV4 ተሽከርካሪን በሁለተኛ ዙር በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል። በዚህም መሠረት በጨረታው ላይ ለመሳተፍ የሚፈልጉና ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያመሟሉ ማንኛውም ተጫራቾች ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 (አስር) ተከታታይ ቀናት መጫረት ይችላሉ፡፡
- ማንኛውም የመጫረት ፍላጎት ያለው በጨረታው ላይ መሳተፍ ይችላል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን ሲያቀርቡ ለተጫረቱበት ተሸከርካሪ የጨረታ ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋውን 10% (አስር በመቶ) በባንክ በተመሰከረለት ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል። ከሲፒኦ ውጪ የሚያቀርቡ የጨረታ ማስከበሪያ ተቀባይነት የለውም።
- የጨረታ ሰነዱን የገዙ ተጫራቾች ተሽከርካሪው አ/አ ቦሌ መድሀኒአለም ሂድሞና ህንፃ 4ኛ ፎቅ በሚገኘው የድርጅቱ ቢሮ ተሽከርካሪ ማቆሚያ ቦታ በአካል በመቅረብ ማየት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ከጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ሲፒኦ አሸናፊው ተለይቶ ከታወቀ በኋላ የሚመለስ ይሆናል፡፡
- የጨረታው አሸናፊ ለተሽከርካሪው የሚከፈሉ ማንኛውንም የመንግስት ከፍያዎችን ሁሉ ይሸፍናል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች ሌሎች በሰጡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችልም፡፡
- የጨረታው አሸናፊ መሆኑ የተገለፀለት ተጫራች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው 10% (አስር በመቶ) እንደውል ማስከበሪያ ይቆጠራል ፡፡ የጨረታው አሸናፊ የገባውን ውል ካልፈፀመ ለጨረታ ማስከበሪያ የተያዘውን ዋስትና እንደ ውል ማስከበሪያ ተቆጥሮ የተያዘውን ገንዘብ አልቪማ የምግብ አምራች ኃ/የተ/የግ/ማህበር ወደ ራሱ ካዝና ገቢ ያደርጋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከድርጅቱ ፋይናንስ መምሪያ አዳማ ወይንም አዲስ አበባ ከሚገኘው ቢሮ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት እለት አንስቶ ለ10 (አስር) ተከታታይ ቀናት እየር ላይ ቆይቶ በ11 ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በተመሳሳይ ቀን አዲስ አበባ ከተማ በሚገኘው የድርጅቱ ቢሮ ከጠዋቱ በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከላይ በተጠቀሰው ቀን እና ሰዓት ለጨረታ ሰነድ ማስገቢያ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡ በጨረታ ሰነዱ ላይ ያልተሞላ ወይንም በሌላ ወረቀት ላይ የተሞላ ዋጋ ተቀባይነት የለውም፡፡
- የጨረታው አሸናፊ የሚለየው ባቀረበው የመግዣ ዋጋ መሠረት ብቻ ነው::
- የጨረታው አሸናፊ ጨረታውን ማሸነፉ በተገለጸ በ7 ቀናት ውስጥ በአካል ቀርቦ ውል መፈፀም አለበት።
- የጨረታው አሸናፊ ውል እንዲፈፅም በተገለፀለት በ 7 ቀናት ውስጥ ቀርቦ ውል ባይፈፅም ድርጅቱ ለጨረታ ማስከበሪያ የተያዘውን ዋስትና ወደ ራሱ ካዝና ገቢ ያደርጋል፡፡
- ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር ፡- 011-639-2511
አልቪማ የምግብ አምራች ኃ/የተ/የግ/ማህበር
