ኤም ኤስ አይ ኢትዮጵያ የተባለ የግብረሰናይ ድርጅት ሲገለገልባቸዉ የነበሩትን ሶስት ያገለገሉ መኪናዎችን እና አንድ ሞተር ሳይክል ባሉበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
ኤም ኤስ አይ ኢትዮጵያ
ያገለገሉ የተሽከርካሪ ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ
ኤም ኤስ አይ ኢትዮጵያ የተባለ የግብረሰናይ ድርጅት ሲገለገልባቸዉ የነበሩትን ሶስት ያገለገሉ መኪናዎችን እና አንድ ሞተር ሳይክል ባሉበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም ተጫራቾች ፡-
- ማንኛውም ተጫራች ንብረቶቹ በሚገኙበት አድራሻ ሳሪስ ካዲስኮ የቀለበት መንገድ አደባባይ አካባቢ ከበላይ አብ ሞተርስ ዋናዉ ቢሮ ጀርባ በድርጅቱ ማህከላዊ መጋዘን ጊቢ ዉሰጥ ጨረታዉ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10ኛዉ ቀን ባሎት የሥራ ቀናት ከጠዋቱ 3፡00 እስከ ቀኑ 10፡00 ሰዓት ድረስ መመልከት የሚቻል ሲሆን ከ11ኛዉ ቀን እስከ 14ኛዉ ቀን ኮፍን እየከፈቱ ውስጡን ማየት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የሚገዙትን ንብረት ጠቅላላ ዋጋ 20 በመቶ (20%) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒአ (CPO) አሰርተው ከጨረታው መክፈቻ ቀንና ሰዓት በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል። የሚዘጋጀው የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ከአዲስ አበባ ከተማ ውጭ ከሆነ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፎች ብቻ መሆን ይኖርበታል፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትናው ለአሸናፊዎች ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር የሚታሰብ ሲሆን ለተሸናፊዎች የጨረታው ውጤት እንደፀደቀ ይመለስላቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የንብረቶቹን ዝርዝር የያዘው ሠነድ ላይ ያገለገለ አሮጌ መኪና የማጫረቻ ዋጋ ማቅረቢያ ቅፅ የሚገዙበትን ዋጋ በአሃዝና በፊደል ያለ ስርዝ ድልዝ ገልፀው በታሸገ ኤንቬሎፕ /ፖስታ/ በአዲስ አበባ ከተማ (ቂርቆስ ክ/ከተማ፣ ወረዳ 02፣ የቤት ቁጥር 174) በወሎ ሰፈር፣ ተባበር በርታ ህንጻ (ሰፈር) አካባቢ፣ ዳኒ ፕላዛ ህንጻ ጀርባ በሚገኘው የድርጅቱ ህንጻ ሁለተኛ ፎቅ፣ የግዢ ከፍል በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ነገር ግን የሚሰጡት ዋጋ ላይ ስርዝ ድልዝ ካለ ከጎኑ በተጫራቹ መፈረም ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቾች ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስራ ስድስት /16/ ተከታታይ ቀናት ውስጥ የጨረታውን ሰነድ ማስገባት አለባቸው::
- አሸናፊ ተጫራቶች ጨረታውን ማሸነፋቸው ከተገለፀላቸው ቀን ጀምሮ በሶስት /3/ ቀናት ውስጥ ገንዘቡን ገቢ በማድረግ በአስር /10/ ቀናት ውስጥ ንብረቱን የመረከብ እና የማንሳት ግዴታ አለባቸው፡፡ ይህ ካልሆነ ያስያዙት ገንዘብ ለድርጅቱ ገቢ ሆኖ ተሸከርካሪዉ በድጋሜ ለጨረታ ሊቀርብ ይችላል፡፡
- ተጫራቾች ከድርጅቱ ግዥ ክፍል የንብረቶቹን ዝርዝር መረጃ የያዘ የተጫራቾች መመሪያ እና የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ለተሽከርካሪዎቹ የማይመለስ ብር 500 /አምስት መቶ ብር/ እየከፈሉ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስራ አራት /14/ ተከታታይ ቀናት ዉስጥ ከድርጅቱ እንግዳ መቀበያ ክፍል መግዛት ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ሳጥኑ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ላሉት አስራ ስድስት /16/ ተከታታይ ቀናት ክፍት ሆኖ መጋቢት 02 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያው ቀን 4፡30 ተጫራቾቹ ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙብት በአዲስ አበባ ከተማ (ቂርቆስ ክ/ከተማ፣ ወረዳ 02፣ የቤት ቁጥር 174) በወሎ ሰፈር፣ ተባበር በርታ ህንጻ (ሰፈር) አካባቢ፣ ዳኒ ፕላዛ ህንጻ ጀርባ በሚገኘው የድርጅቱ ህንጻ አንደኛ ፎቅ፣ በሚገኘው የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች ስለ አሻሻጡ ዝርዝር ሁኔታ ከጨረታው ሰነዱ ላይ የተጫራቾች መመሪያ ላይ ማግኘት ይችላሉ።
- ድርጅቱ ለአሻሻጡ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 0115509251፣ 0115509307 ወይም 0115152157 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
ኤም ኤስ አይ ኢትዮጵያ
