የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት የወላይታ ዞን አረካ ከተማ ፋይ/ጽ/ቤት በ2017 በጀት ዘመን በመደበኛ ፕሮግራም የሚሠሩ የመሠረተ ልማት ግንባታ ሥራዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሠራት ይፈልጋል።
በወላይታ ዞን አረካ ከተማ አስ/ር ፋይናንስ ጽ/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት የወላይታ ዞን አረካ ከተማ ፋይ/ጽ/ቤት በ2017 በጀት ዘመን በመደበኛ ፕሮግራም የሚሠሩ የመሠረተ ልማት ግንባታ ሥራዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሠራት ይፈልጋል። በዚህ መሠረት:-
- የጤና ጣቢያ ፋርማሲ፣ ጥበቃ ቤት እና የሽንት ቤት ግንባታ ግዥ
በዚህ መሠረት ተወዳዳሪዎች ማሟላት የሚጠበቅባቸው፡
- በኮንስትራክሽን ሚኒስቴር የተመዘገበ ደረጃቸው GC/BC 8 በኮንስትራክሽን ዘርፍ ደረጃ የተሰማሩ
- በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያለው እና ኦሪጅናል መረጃ ማቅረብ የሚችል
- የ2017ዓ.ም ግብር ከፍሎ የንግድ ፈቃድ ያሳደሰ
- የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያለው
- ቲን ሠርቴፊኬት ያለው
- ቫት ተመዝጋቢ የሆነ
- በOnline አቅራቢነት E-GP የተመዘገበ እና የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 270,000.00 (ሁለት መቶ ሰባ ሺህ) ብር፣ በባንክ የተረጋገጠበት ቼክ (ሲ.ፒ.ኦ)፤ በጥሬ ገንዘብ /በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና /በባንክ/ የተረጋገጠ ሌተር ኦፍ ክሬዲት/ ማቅረብ ይኖርባችኋል፡፡
- ተጫራቹ ይህ ማስተወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 30 ተከታታይ ቀናት ውስጥ የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር ብቻ/ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ከአረካ ከተማ ፋይናንስ ጽ/ቤት በፑል ማዕከል መግዛት የሚትችሉ መሆኑን እየገለጽን የአንዱንና ጠቅላላ ዋጋ በጨረታ ሰነድ ላይ በመሙላት ለዚሁ አገልግሎት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በሰም የታሸገ ፖስታ አንድ ኦሪጂናል እና ሁለት ኮፒ በአንድ እናት ፖስታ ውስጥ በማሸግ ማቅረብ የሚቻል ሲሆን ጨረታው የሚከፈተው በ31ኛው ቀን ዕለቱ የሥራ ቀን ከሆነ ከጧቱ 4፡00 ታሽጎ በዕለቱ 4፡30 ይከፈታል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡
- ተጫራቾች ያለመገኘታቸው የጨረታ ሂደቱን እያስተጓጉልም፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0465520800/0241 መነጋገር ይችላሉ
በወላይታ ዞን የአረካ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት
