የጅማ መምህራን ት/ኮሌጅ በ2017 የበጀት ዓመት የኤሌክትሪከ ወፍጮ (በአውሮፓ ስታንዳርድ የተመረተ) እና አንደኛ ደረጃ ንጹህ የተለቀመ ዛላ በርበሬ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የጅማ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የግልጽ ጨረታ ቁጥር 001/2017
የጅማ መምህራን ት/ኮሌጅ በ2017 የበጀት ዓመት የኤሌክትሪከ ወፍጮ (በአውሮፓ ስታንዳርድ የተመረተ) እና አንደኛ ደረጃ ንጹህ የተለቀመ ዛላ በርበሬ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ከዚህ ቀጥሎ የተዘረዘሩትን መሥፍርቶች የሚያሟሉ በጨረታው ተሳታፊ መሆን ይችላሉ።
በዚህ መሠረት ጨረታው ላይ መሳተፍ ለሚፈልጉ ተጫራቾች፡-
- በዘመኑ አግባብነት ያለው የታደሰ የንግድ ፍቃድ፤ የንግድ ምዝገባ ሰርተፍኬት ያላቸው፤ የግብር ከፋይነት የምስክር ወረቀት ፤ የቫት ምስክር ወረቀት እና የአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡት ምስክር ወረቀት ኦርጅናልና ኮፒውን ጎን ለጎን ማቅረብ የሚችሉ።
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ዕለት 7 ጀምሮ የኤሌክትሪክ ወፍጮ (በአውሮፓ ስታንዳርድ የተመረተ) እና አንደኛ ደረጃ ዛላ በርበሬን ሰነድ በግል የማይመለስ የኢትዮጵያ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር ብቻ) ለየብቻ ለኤሌክትሪክ ወፍጮ (በአውሮፓ ስታንዳርድ የተመረተ) እና ለአንደኛ ደረጃ ንጹህ የተለቀመ ዛላ በርበሬ ኦሮሚያ ህብረት ሥራ ባንክ ጅማ ቅርንጫፍ በሂሳብ ቁጥር 1000064416026 ገቢ በማድረግ የጨረታ ሰነዶችን ከጅማ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ ቢሮ ቁጥር 009 መግዛት የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 2% በባንክ የተመሰከረለትን ሲፒኦ (CPO) ለእያንዳንዱ ሰነድ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታው ሰነዶች ሽያጭ ቀን 18/6/2017 እስከ 8/7/2017 ይሆናል፡፡
- የጨረታ ሣጥን መክፈቻ ቀን እና ሰዓትን አስመልክቶ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ተከታታይ ባሉት የሥራ ቀናት ውስጥ በማስገባት በ21ኛ የሥራ ቀን 8/7/2017 ከጠዋቱ እስከ 4፡00 ሰዓት አጠናቆ በማስገባት ታሽጎ በ4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኮሌጁ እቅድ ፣ ፋይናንስ እና ንብረት አስተዳደር ቢሮ ቁጥር 009 በግልፅ ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት አንደኛ ደረጃ ዛላ በርበሬን ናሙና ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- አሸናፊው ተጫራች ያሸነፈበትን የኤሌክትሪክ ወፍጮ (በአውሮፓ ስታንዳርድ የተመረተ) ጅማ መምህራን ት/ምህርት ኮሌጅ ድረስ የጭነትና የትራንሰፖርት ወጭውን ችሎ በመምጣት ተክሎ ስራ አስጀምሮ ማስረከብ አለበት።
- አሸናፊው ተጫራች አንደኛ ደረጃ ንጹህ የተለቀመ ዛላ በርበሬ ጅማ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ ድረስ የጭነትና የትራንሰፖርት ወጭውን ችሎ በመምጣት ማስረከብ አለበት፡፡
- ኮሌጁ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 0966-566646 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የጅማ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ
