Tender Detail

Tender Details

  • Company በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት በጎፋ ዞን ጤና መምሪያ የሣውላ አጠቃላይ ሆስፒታል
  • Address ጎፋ ዞን: ደቡብ ፡ ኢትዯጵያ, Phone: 0919703532
  • Website
  • Deadline09 Mar 2025, 9:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Medical Equipment And Supplies

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ጤና ቢሮ በጎፋ ዞን ጤና መምሪያ ሣውላ አጠቃላይ ሆስፒታል በ2017 በጀት ዓመት የህክምና መገልገያ ዕቃዎችን Medical equipment spare part accessorey በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት በጎፋ ዞን ጤና መምሪያ የሣውላ አጠቃላይ ሆስፒታል


 

የጨረታ ማስታወቂያ

 

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ጤና ቢሮ በጎፋ ዞን ጤና መምሪያ ሣውላ አጠቃላይ ሆስፒታል በ2017 በጀት ዓመት የህክምና መገልገያ ዕቃዎችን Medical equipment spare part accessorey በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

በዚህ መሠረት ከዚህ በታች የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እየገለጽን

  1. በዘርፉ የተሰማሩ የንግድ ፍቃድ ያለው/ያላት
  2. 2017 ዓ.ም የታደሰ የንግድ ፍቃድ ማቅረብ የሚችል/ የምትችል
  3. የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል/ የምትችል ፣
  4. የቫት ተመዝጋቢ የሆነ/ች
  5. የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር /TIN NO/ ያለው/ያላት፣
  6. 2016 ዓ/ም ግብር ከፍሎ ያጠናቀቀ/ች
  7. አቅራቢነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል/ የምትችል
  8. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚወዳደሩበትን የሽያጭ ጠቅላላ ዋጋ 2% በባንክ የተረጋገጠ ቼክ ወይም CPO ማቅረብ አለባቸው::
  9. የጨረታ ሰነድ በብር 200 (ሁለት መቶ) ብር ብቻ ጨረታው ከወጣበት ቀን እስከ 15ኛው ቀን 11፡30 ሰዓት ድረስ ባሉት ተከታታይ የመንግስት የስራ ቀናት ውስጥ ቢሮ ቁጥር - 6 በመቅረብ መግዛት ይችላሉ ::
  10. የጨረታ ሠነድ ኦርጅናል እና የማይመለስ በአንዳንድ ገጽ ወረቀት ኮፒ በማድረግ በተለያዩ ፖስታ በማሸግ በአንድ እናት ፖስታ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  11. ጨረታው የሚከፈተው በ16ኛ ቀን 3፡00 ሰዓት ታሽጎ 3፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሲሆን ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙ ጨረታውን መክፈት እያስተጓጉልም ፡፡
  12. አሸናፊው ተጫራች ያሸነፈውን ዕቃ እስከ ተቋሙ ድረስ በማምጣት ማስረከብ ይኖርበታል።
  13. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
  14. ተጫራቾች ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 6 በአካል በመቅረብ ወይም በስልከ ቁጥር- 0913070604 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡

 

ማሳሰቢያ ፡- የጨረታ መዝጊያና መከፈቻ ቀን እሁድና ቅዳሜ ወይም ህዝባዊ በዓል ባለበት ቀን ላይ ከዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ተዘግቶ በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል ::

 

 

በጎፋ ዞን ጤና መምሪያ የሣውላ አጠቃላይ ሆስፒታል

 

Save Tender