በባሌ ዞን የሲናና ግብርና ምርምር ማዕከል በ2016 በጋ ወቅት ያመረታቸውን የተለያዩ የስንዴ ዝርያ ብዛት በኩንታል 374.06 (ሶስት መቶ ሰባ አራት ከ 06 ኩንታል) በማሽን ተበጥረው ንፁህ ለምግብና ለፋብሪካ የሚውሉ የተለያዩ የፓስታ እና የማካሮኒ ስንዴ ዝርያ ዓይነቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል ::
በባሌ ዞን የሲናና ግብርና ምርምር ማዕከል
ለሶስተኛ ጊዜ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 01/213/2017
በባሌ ዞን የሲናና ግብርና ምርምር ማዕከል በ2016 በጋ ወቅት ያመረታቸውን የተለያዩ የስንዴ ዝርያ ብዛት በኩንታል 374.06 (ሶስት መቶ ሰባ አራት ከ 06 ኩንታል) በማሽን ተበጥረው ንፁህ ለምግብና ለፋብሪካ የሚውሉ የተለያዩ የፓስታ እና የማካሮኒ ስንዴ ዝርያ ዓይነቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል :: ስለዚህ በሰነድ ውስጥ የተጠቀሱትን እና ከዚህ ቀጥሎ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ የምግብ ኮምፕሌክስ ፋብሪካ ባለቤቶች ፤ መንግስታዊ ወይም መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች፤ ግለሰብ ነጋዴዎች በጨረታው መወዳደር ይችላሉ ።
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት የሥራ ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት የማይመለስ የሰነድ መሸጫ ዋጋ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) Oromia Agricultural Research Institute Internal Revenue B ስም በተከፈተው የባንከ ሂሳብ ቁጥር 1000466928357 ኢትዮጰያ ንግድ ባንክ በማስገባት ሰነዱን ከባሌ ዞን ገንዘብ ጽ/ቤት ከቢሮ ቁጥር 15 መግዛት የሚችሉ ሲሆን ፡ ተጫራቾች ለሚጫረቱባቸው የስንዴ ዝርያዎች ዓይነት ከጠቅላላ ዋጋ ላይ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 20 % ( 20 ፕርሰንት ) የያዘ ሲፒኦ ብቻ የሲናና ግብርና ምርምር ማዕከል ስም በማስያዝ መወዳደር ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት የስራ ቀን ጀምሮ የሚጫረቱበን ሰነድ በመግዛት 1ኛ, ኦሪጂናል የመወዳደሪያ ዋጋ የተሞላበት ሰነድ እና 2ኛ ዋጋ የተሞላበት ኮፒ ሰነድ ሁለቱንም ሰነድ በተለያዩ ፖስታዎች አሽገው ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ዘወትር በስራ ሰአት የጨረታው ሳጥን እስከሚታሸግበት እለት እና ሰአት ድረስ ማስገባት ይችላሉ ::
- ተጫራቾች በመወዳደሪያ ሰነዶቻቸው ላይ የድርጅታቸውን ወይም የግለሰቡን/የነጋዴውን ስም እና ሙሉ አድራሻ ስልከ ቁጥር በመፃፍ መፈረም ይኖርባቸዋል ፡፡
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ በሲናና ግብርና ምርምር ማዕከል ስም ያስያዙትን ሲፒኦ ኦሪጂናል የመወዳደሪያ ዋጋ የተሞላበት ሰነድ ጋር በፖስታ አሽገው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- በእያንዳንዱ የመወዳደሪያ ሰነድ እና የታሸገ ፖስታ ላይ የድርጅቱ ኃላፊ ፊርማ እና ማህተም መኖር አለበት።
- ጨረታው በማስታወቂያ ከወጣበት በ16ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በባሌ ዞን ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 15 ይከፈታል፡፡ ዕለቱ በዓል ወይም ዝግ ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን ጨረታው ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች ማሸነፋቸው በደብዳቤ ከተገለፀላቸው ከ5ኛው ቀን በኋላ ከ6ኛው ቀን ጀምሮ በ7 የስራ ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ጠቅላላ ዋጋ በመክፈል ስንዴውን መረከብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
- ማዕከሉ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልከ ቁጥር 022-665-0225/0930292332 ደውለው ይጠይቁ።
በባሌ ዞን የሲናና ግብርና ምርምር ማዕከል
