በግንቦት 20 2ኛ ደረጃና መሰናዶ ት/ቤት ፋይናንስ ግዥና ንብረት አስተዳደር ደጋፊ የሥራ ሂደት በ2017 ዓ.ም ከመደበኛ እና ከውስጥ በጀት ደረጃቸውን የጠበቁ አርጅናል የሆኑ ሎት 1፡- ቋሚና አላቂ የጽሕፈት መሣሪያ:- ሎት 2፡- የጥገና አገልግሎት የግንብ አጥር ጥገና) በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ የግንቦት 20 2ኛ ደረጃና መሰናዶ ት/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ግዥ ቁጥር 002/2017
በግንቦት 20 2ኛ ደረጃና መሰናዶ ት/ቤት ፋይናንስ ግዥና ንብረት አስተዳደር ደጋፊ የሥራ ሂደት በ2017 ዓ.ም ከመደበኛ እና ከውስጥ በጀት ደረጃቸውን የጠበቁ አርጅናል የሆኑ ሎት 1፡- ቋሚና አላቂ የጽሕፈት መሣሪያ:- ሎት 2፡- የጥገና አገልግሎት የግንብ አጥር ጥገና) በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በዚህም መሰረት ቀጥሎ የተጠቀሱትን መስፈርቶች የምታሟሉ አቅራቢ ድርጅቶች በጨረታ እንድትወዳደሩ እንጋብዛለን፡፡
- ከመንግሥት ግዥ ኤጀንሲ ወይም ከፋይናስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ዌብ ሳይት ላይ በዘርፉ የአቅራቢነት ምዝገባ የተመዘገበ፣ በዘርፉ ሕጋዊ የታደሰና ከሚያቀርቡት ዕቃ ወይም አገልግሎት ጋር ተዘማጅነት ያለው የንግድ ፈቃድ የዘመኑን ግብር የከፈሉ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑና የታክስ ከፋይነት ቲን ቁጥር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ሎት 1 ብር አስር ሺህ ብር፣ ሎት2 ብር 5000 /አምስት ሺህ ብር/ በባንክ የተረጋገጠ CPO በት/ ቤቱ ስም ተሠርቶ ማስገባት ይኖርባችኋል፡፡
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት የማይመለስ 150 /አንድ መቶ ሀምሳ ብር / በመክፈል ሰነዱን መውሰድ ትችላላችሁ::
- የጨረታ ሳጥኑን በ10ኛው የሥራ ቀን ከቀኑ 11፡30 ሰዓት ታሽጎ በቀጣዩ 11ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ አሸናፊ ሆነው የተገኙባቸውን ዕቃዎች ከአጠቃላይ ዋጋ 10% ውል ማስከበሪያ በማስያዝ ከት/ቤቱ ጋር የግዥ ውል ስምምነት መፈጸም ይኖርባቸዋል፡፡
- መሥሪያ ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ - የት/ቤቱ አድራሻ ሳሪስ ከዳማ ሆቴል ወደ ሃና በሚስደው አስፋልት ከኮከብ ፓስታና ዱቄት ፋብሪካ ከፍ ብሎ ከአስፋልት 200 ሜትር ገባ ብሎ ነው::
ስልክ ቁጥር - 011-419 -80 -66/011 419 -1505
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትም/ቢሮ የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ የግንቦት 20 2ኛ ደረጃና መሰናዶ ት/ቤት
