Tender Detail

Tender Details

  • Company በምስ/ጎጃም ዞን የአዋበል ወረዳ ገንዘብ ፅ/ቤት
  • Address ምስራቅ ጎጃም : አማራ ክልል ፡ ኢትዯጵያ, Phone: 0587720630
  • Website
  • Deadline05 Mar 2025, 9:30 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Building Materials

በአብክመ በምስ/ጎ/ዞን አዋበል/ወረዳ/ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት ለተለያዩ ሴ/መ/ቤቶች በ2017 በጀት አመት አገልግሎት የሚውል ከመደበኛ በጀት ከዚህ በታች የተዘረዘሩ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በምስ/ጎጃም ዞን የአዋበል ወረዳ ገንዘብ ፅ/ቤት


 

ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

 

በአብክመ በምስ/ጎ/ዞን አዋበል/ወረዳ/ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት ለተለያዩ ሴ/መ/ቤቶች በ2017 በጀት አመት አገልግሎት የሚውል ከመደበኛ በጀት ከዚህ በታች የተዘረዘሩ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ሎት 1 ድጋሚ የወጣ የፅህፈት መሳሪያ : ሎት2 የኮንስትራክሽን ዕቃዎች ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን ::

  1. በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው::
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/ ያላቸው።
  3. የጨረታ ተሳታፈዎች የሚሙሉት ዋጋ ከ200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የቫት /VAT/ ተመዝጋቢ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተ/ቁ 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸው ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው::
  5. የሚገዙ ዕቃዎችን አይነትና ዝርዝር መግለጫ እስፔስፍኬሸን ከእያንዳንዱ ሎት ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የመሸጫ ዋጋ 100 /አንድ መቶ ብር/ የማይመለስ ብር በመክፈል ቢሮ ቁጥር 03 መግዛት ይቻላል፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሎት 1 ብር 15,000 /አስራ አምስት ሺህ ብር/ እና ሎት 2 ብር 10,000 /አስር ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ ትዕዛዝ /ሲ.ፒ.ኦ/ ወይም በመሂ አንድ ማስያዝ አለባቸው::
  8. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆነ ሁለት ቅጅዎች እና ዋና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በወጣው ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን ድረስ በጽ/ቤቱ በግዥ ቡድን ወይም ቢሮ ቁጥር 05 በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት እስከ 3:30 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  9. ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም በግዥ ቡድን ቢሮ ቁጥር 05 በ16ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ይከፈታል፡፡
  10. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
  11. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 05 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0587720630/0004 በመደወል ማግኘት የሚችሉ ሲሆን ጨረታው ሲከፈትም ሆነ ከተከፈተ በኋላ የሚገኝ ከጥቃቅን ስህተቶች በስተቀር ከባድ ስህተቶች ተቀባይነት የላቸውም፡፡
  12. መ/ቤቱ ጨረታውን 20% የመቀነስ ወይም የመጨመር መብቱ የተጠበቀ ነው ::
  13. የእቃውን ዋጋ የሚሞላው ከጨረታው ጋር በምናቀርበው ስፔስፊኬሽን መሰረት ሆኖ ስፔስፊኬሽን ቀይሮ መሙላት የተከለከለ ነው::
  14. ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በበዓል ቀን ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን ይከፈታል፡፡
  15. አሸናፊው ያሸነፋቸውን እቃዎችን አዋ/ወ/ገንዘብ/ጽ/ቤት ድረስ ያለማንጠባጠብ አጠቃሎ ማቅረብ ይጠበቅበታል::
  16. አሸናፊው በሎት ይለያል በሎቱ ውስጥ የተጠቀሱት ዝርዝሮች በሙሉ ዋጋቸው መሞላት ይኖርባቸዋል፡፡
  17. ናሙና ለሚያስፈልጋቸው እቃዎች ናሙናውን አዋ/ወ/ገንዘብ/ጽ/ቤት በግዥ ቢሮ ቁጥር 05 ማግኘት ይችላሉ።
  18. ማንኛውም የሚቀርበው እቃ ኦርጅናልና ጥራቱ የተጠበቀ መሆን አለበት፤

 

በምስ/ጎጃም ዞን የአዋበል ወረዳ ገንዘብ ፅ/ቤት

 

Save Tender