ደ/ኢ/መንግስት መስኖና ቆላማ አካባቢ ልማት ቢሮ በደቡብ ኦሞ ዞን ዳሰነች ወረዳ ለሚያስገነባው ማህበራዊ ተቋማት ግንባታ ሥራን ሕጋዊ ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል፡፡
SOUTH ETHIOPIA IRRIGATION AND LOWLAND AREA DEVELOPMENT BUREAU (የደቡብ ኢትዮጵያ መንግስት መስኖና ቆላማ አካባቢ ልማት ቢሮ)
የጨረታ ማስታወቂያ
ደ/ኢ/መንግስት መስኖና ቆላማ አካባቢ ልማት ቢሮ በደቡብ ኦሞ ዞን ዳሰነች ወረዳ ለሚያስገነባው ማህበራዊ ተቋማት ግንባታ ሥራን ሕጋዊ ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል፡፡
በዚሁ መሠረት -
- ደረጃቸው GC/6 እና ከዛ በላይ ያለ ሥራ ፍቃዳቸውንና የምዝገባ ሠርተፍኬታቸውን ለ2017 ዓ.ም ያሳደሱ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸውና ለተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡና የታክስ መለያ ቁጥር ያላቸው፣
- ፍቃዳቸውንና የምዝገባ ሠርተፍኬታቸውን ለ2017 ዓ.ም ያሳደሱ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው ተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡና የታክስ መለያ ቁጥር ያላቸው
- ተጫራቾች ለሥራው የተዘጋጀውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ30 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ለእያንዳንዱ ዶክመንት የማይመለስ ብር 1000 /አንድ ሺህ ብር/ በመክፈል ዘወትር በሥራ ቀናት በቢሮ የግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ዋስትና 250,000 /ሁለት መቶ ሃምሣ ሺህ ብር/ በባንክ የተረጋገጠ ቼክ /CPO/ ወይም ባንክ ዋስትና ከቴክኒካል ኦሪጅናል ሰነድ ጋር አሽገው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን ቴክኒካልና ፋይናንሻል ዶክመንት ኦርጅናል እና ሁለት ሁለት ፎቶ ኮፒ እያንዳንዳቸው ለየብቻ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ እና ጠቅላላውን በአንድ በሰም በታሸገ ኤንቨሎኘ በማድረግ/ በ31ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00-6፡00 ሰዓት ቢሮው ለዚሁ ባዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ መክተት አለባቸው።
- ጨረታው በ31ኛው ቀን ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ተጫራቾችና ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- 31ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል፡፡
- ቢሮው ጨረታውን በመሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ተጨማሪ መረጃ ከሰነዱ ማግኘት የሚቻል መሆኑን እያሳወቅን የዴ/ኢ/ክ/መንግስት እንደገና ተሻሽሎ በወጣው የግዥ አፈጻጸም መመሪያ ቁጥር 70/2017 እና በመመሪያው ላይ የተደረገውን ማብራሪያ ወይም ማሻሻያ ሰርኩላር ተፈጻሚ ይደረጋል፡፡
በደ/ኢ/ክ/መንግስት
መስኖና ቆላማ አካባቢ ልማት ቢሮ
ጂንካ፤
