Tender Detail

Tender Details

  • Company Development Bank of Ethiopia (የኢትዮጵያ ልማት ባንክ)
  • Address ካዛንቺስ ሾንጌ ህንጻ 2ኛ ፎቅ ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0115 57 80 88
  • Websitehttps://dbe.com.et/
  • Deadline17 Mar 2025, 2:00 PM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Machinery Spare Parts

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ መነሻ ግምታቸው ብር 11,643.481.64 /አስራ አንድ ሚሊየን ስድስት መቶ አርባ ሶስት ሺህ አራት መቶ ሰማንያ አንድ ብር ከ64/100 ሳንቲም/ የሆኑ እርሻ መሣሪያ መለዋወጫ ዕቃዎችን ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡

Development Bank of Ethiopia (የኢትዮጵያ ልማት ባንክ)


 

የጨረታ ማስታወቂያ

 

  1. የኢትዮጵያ ልማት ባንክ መነሻ ግምታቸው ብር 11,643.481.64 /አስራ አንድ ሚሊየን ስድስት መቶ አርባ ሶስት ሺህ አራት መቶ ሰማንያ አንድ ብር ከ64/100 ሳንቲም/ የሆኑ እርሻ መሣሪያ መለዋወጫ ዕቃዎችን ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
  2. ተጫራቾች የእርሻ መሣሪያ መለዋወጫ ዕቃዎች ዝርዝር የያዘውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በባንኩ አንደኛ ፎቅ ኮርፖሬት ቅርንጫፍ በመክፈል ከባንኩ ሶስተኛ ታወር አንደኛ ፎቅ ፋሲሊቲ ማኔጅመንት ዳይሬክቶሬት ቢሮ መውሰድ ይችላሉ፡፡
  3. ተጫራቾች የሚገዙበትን ዋጋ በመጥቀስና የታደሰ የነዋሪነት መታወቂያ በመያዝ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ዋናው መስሪያ ቤት ሁለተኛ ታወር መግቢያ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ እስከ መጋቢት 8 ቀን 2017 ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይችላሉ፡፡
  4. የጨረታ ሳጥኑ መጋቢት 8 ቀን 2017 ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት መጋቢት 8 ቀን 2017 ከቀኑ 8፡05 ይከፈታል፡፡
  5. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልግ በቅድሚያ የመነሻ ዋጋውን 25% /ሃያ አምስት በመቶ/ በገንዘብ ክፍያ ማዘዣ /ሲፒኦ/ ማስያዝ አለበት፡፡
  6. አሸናፊው ያስያዘው ገንዘብ ከግገዢው ዋጋ ጋር ሲታሰብለት ለተሸነፉት ያስያዙት ገንዘብ ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል፡፡
  7. የጨረታው አሸናፊ ማሸነፉ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር 10 ተከታታይ ቀናት የገዛበትን ገንዘብ ሙሉ በሙሉ ከፍሎ የእርሻ መሣሪያ መለዋወጫዎቹን መረከብ ይኖርበታል፡፡ ይህ ካልሆነ ጨረታው ተሰርዞ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ሙሉ በሙሉ ለባንኩ ገቢ ይሆናል፡፡
  8. ገዢው በገዛበት ዋጋ ላይ የተጨማሪ እሴት ታክስ 15% /አስራ አምስት በመቶ/ መክፈል ይጠበቅበታል፡፡
  9. ተጨማሪ መረጃ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ 011-551-11-88 የውስጥ መስመር 726/218 ደውሎ ማግኘት ይቻላል፡፡
  10. ተጫራቶች የእርሻ መሣሪያ መለዋወጫ ዕቃዎቹን መመልከት ከፈለጉ ቃሊቲ በሚገኘው የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ዊርቱ መጋዘን ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ረቡዕ እና አርብ ከጠዋቱ 2፡30- 6፡00 ከሰዓት ከ7፡00-10፡30 ሰዓት በአካል በመገኘት መመልከት ይችላሉ፡፡
  11. ባንኩ ስለ መለዋወጫዎቹ አሻሻጥ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

 

 

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ

 

Save Tender