የጋምቤላ አነስተኛ ብድርና ቁጠባ ተቋም በ2017 በጀት ዓመት የትራክተር ዕቃዎች /ACCESSORIES/ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
የጋምቤላ አነስተኛ ብድርና ቁጠባ ተቋም
የጨረታ ማስታወቂያ
የጋምቤላ አነስተኛ ብድርና ቁጠባ ተቋም በ2017 በጀት ዓመት የትራክተር ዕቃዎች /ACCESSORIES/ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በዚህም መሠረት ፡-
- ማረሻ ባለ6 በልደን ሞዴል ብዛት 9
- መከስከሻ ባለ24 ሚጣድ በልደን ሞደል ብዛት 9
- ፕላንተር/መዝሪያ Disk6 AGROMASTER ብዛት 9
በዘርፉ ፈቃድ ያላቸውን እና ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተወዳዳሪዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ ለመፈጸም ይፈልጋል፡፡
በዚሁ መሠረት፡-
- በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ፎቶ ኮፒ፣
- የአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ ስለመመዝገባቸው የሚገልጽ ከመንግሥት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ የተሰጠንን የምዝገባ ምስክር ወረቀት ፎቶ ኮፒ፣
- የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር የምስክር ወረቀት ፎቶ ኮፒ
- ከ2017 ዓ.ም ውዝፍ ግብር ነፃ ስለመሆኑ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆነ
- ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ ቀናት ተጫራቾች ለዚሁ የተዘጋጀውን የጨረታ ሠነድ የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል በጋምቤላ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት የጋምቤላ አነስተኛ ብድርና ቁጠባ ተቋም ቢሮ ግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ዳይ በመቅረብ መግዛት የምትችሉ መሆኑ፤
- ተጫራቾች የጨረታውን ዋስትና ማስከበሪያ ብር 150,000 /አንድ መቶ ሃምሳ ሺህ/ ብር በሲፒኦ ወይም በባንክ ጋራንቲ ወይም በቼክ ከጨረታ ሠነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን ዋናውን እና ኮፒ ለየብቻ በሰም በማሸግ እስከ 10ኛው ቀን በ3:30 እስከ 4፡30 ድረስ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብት የተጠበቀ ነው::
- ውል ገብተው ከ10 እስከ 15 ቀን ድረስ ዕቃውን ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት፡፡
- ለተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር 047-551-1250/251977 483 813/251 917 526 665/ መጠቀም የምትችሉ መሆኑን እናስታውቃለን፡፡
የጋምቤላ አነስተኛ ብድርና ቁጠባ ተቋም
