በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ ንብረትነቱ የተለያዩ የኦሮሚያ መ/ቤቶች ከአገልግሎት ዉጭ የሆኑ በቢሮ ዞን ከተማና ወረዳ የሚገኙ የተለያዩ ተሽከርካሪዎች፣ ሞተር ሳይክሎች እና የመኪና ጎማዎች እና ጀነሬተር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
Oromia Public Procurement & Property Disposal Agency (የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ)
ግልጽ የሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር 11/2017
በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ ንብረትነቱ የተለያዩ የኦሮሚያ መ/ቤቶች ከአገልግሎት ዉጭ የሆኑ በቢሮ ዞን ከተማና ወረዳ የሚገኙ
- የተለያዩ ተሽከርካሪዎች፣
- ሞተር ሳይክሎች፣
- የመኪና ጎማዎች እና ጀነሬተር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ በጨረታው ለመወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ መጋቢት 03/2017 ዓ.ም ድረስ ሰነዱን መግዛት የምትችሉ ሲሆን፤
- የኤጀንሲዉ አድራሻ ፤አዲስ አበባ፤ ልደታ ክፍለ ከተማ ባልቻ ሆስፒታል ጀርባ/የኢትዮጲያ ፖሊስ ሆስፒታል ፊትለፊት/ ጨፌ አናኒ ህንጻ ከሚገኘዉ የኤጀንሲው የግዢ፣ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት 3ኛ ፎቅ (3 Floor) ቢሮ ቁጥር-03 በመቅረብ የማይመለስ ብር 300.00/ሦስት መቶ ብር ብቻ/በመክፈል የጨረታ ሠነዱን ከመንግስት ንብረት ዋጋ ግምትና ሽያጭ ዳይሬክቶሬት 3ኛ ፎቅ (3 Floor) ቢሮ ቁጥር-02 መግዛት ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ሰነዱን መግዛት የሚቻለው ዘወትር በሥራ ቀናት ከጠዋቱ 2:30-6፡30 እና ከሰዓት በኋላ ከ7፡30-10፡30 ሰዓት ብቻ ነው::
- የንብረቶቹን ሁኔታ እስከ መጋቢት 03/2017 ዓ.ም ዘወትር በሥራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡30-6፡30 ሰዓት እና ከሰዓት በኋላ ከ7፡30-10፡30 ሰዓት ድረስ በጨረታ ሠነዱ ላይ በተገለፀው ቦታ በመገኘት ማየት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የሚያቀርቡትን ዋጋ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ መጋቢት 04/2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 5፡00 ድረስ በኤጀንሲው ጽ/ቤት ለጨረታው በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው መጋቢት 04/2017 ዓ.ም ከጥዋቱ በ5፡00 ተዘግቶ በዕለቱ በ5፡15 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች ለያንዳንዱ ጨረታ መነሻ ዋጋ 20% /ሃያ ከመቶ/የጨረታ ማስከበሪያ CPO የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ በማዘጋጀትና ከዋጋ ማቅረቢያው ኤንቨሎፕ ውስጥ በመከተት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
CPO ለማሰራት
የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግት የመንግስት
ግዥና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ
Oromia Public Procurement & Property Disposal Agency
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 011-1-8340-636
የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የመንግስት ግዥና ንብረት
ማስወገድ ኤጀንሲ
ፊንፊኔ
