Tender Detail

Tender Details

  • Company የአብክመ/ሰሜን ሸዋ ዞን መንዝ ጌራ ምድር ወረዳ
  • Address ሰሜን ሸዋ : አማራ ክልል ፡ ኢትዯጵያ, Phone: 09-88-82-40-14
  • Website
  • Deadline28 Feb 2025, 5:00 PM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Food And Beverage

የአብክመ ሰሜን ሸዋ ዞን መንዝ ጌራ ምድር ወረዳ የአመድጉያ የበግ ብዜትና ዝርያ ማሻሻያ ማዕከል ግ/ፋ/ን/አስ/ደ/የስራ ሂደት የበጎች የተመጣጠነ መኖ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

የአብክመ/ሰሜን ሸዋ ዞን መንዝ ጌራ ምድር ወረዳ


 

የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

 

የአብክመ ሰሜን ሸዋ ዞን መንዝ ጌራ ምድር ወረዳ የአመድጉያ የበግ ብዜትና ዝርያ ማሻሻያ ማዕከል ግ/ፋ/ን/አስ/ደ/የስራ ሂደት የበጎች የተመጣጠነ መኖ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

እነዚህን ከዚህ በታች ያሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ የንግድ ድርጅቶች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን መ/ቤቱ ይጋብዛል።

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና ማቅረብ የሚችሉ።
  2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ስለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
  3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN Number/ ተመዝጋቢና ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ።
  4. ጠቅላላ ግዥው ወይም ዋጋው ከ200,000/ሁለት መቶ ሺህ ብር እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢና ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
  5. ተጫራቾች በግብርና ሚኒስቴር የእንሰሳት መደሃኒትና መኖ አስተዳደር ቁጥጥር ባለስልጣን የ2017 ዓ.ም የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
  6. ተጫራቾች በገዙት የጨረታ ሰነድ ላይ የመወዳደሪያ ዋጋቸውን በመሙላትና በማሸግ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት በአዲስ አበባ ግብርና ሚኒስቴር ድረስ በመምጣት ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
  7. የሚገዙ ዕቃዎች ዓይነትና ዝርዝር ስፔስፊኬሽን መ/ቤታችን በአማርኛ ቋንቋ ያዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ 50 (ሃምሳ)ብር በመክፈል መግዛት ይችላሉ።
  8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበርያ ዋስትና ቢድ ቦድ/ ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ 2% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ/ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታው ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ የሚችል እና በጨረታው ላይ ችግር ቢከሰትና ጨረታውን ካሸነፈ በኋላ በራሱ ምክንያት ውል ባይፈፅም ያስያዘውን የጨረታ ማስከበሪያ የሚወርስ መሆኑንና አቅርቦቱን ካሸነፈ ለውል ማስከበርያ 10% ማስያዝ የሚችል መሆን አለበት።
  9. ተጫራቾች የተመጣጠነ የበጎች መኖ ዋጋ ሲሞሉ መ/ቤቱ ድረስ የማጓጓዥያ የማስጫኛና የማውረጃ አብሮ መሞላት አለባቸው።
  10. ተጫራቾች የተመጣጠነ የበጎች መኖ የሚጓጓዘው ተወዳዳሪው ድርጅት ካሸነፈበት ቦታ እስከ አመድጉያ የበግ ብዜት ዝርያ ማሻሻያ ማዕከል ድረስ መሆኑን ማወቅ አለባችሁ።
  11. ተጫራቾች የሚመረተው መኖ በንጥረ ምግብ ይዘቱ መሰረት መሆኑንና በላብራቶሪ (ፓስተር) እንደሚታይ(እንደሚመረመር) ማወቅ አለባችሁ።
  12. ተጫራቾች የተመጣጠነ መኖውን ከጨረታ ሰነዱ ማየት ይችላሉ።
  13. አሸናፊው ተጫራች አሸናፊነት ከተገለፀለት ቀን ጀምሮ ከ5 የስራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ቀርቦ የውል ማስከበሪያ 10% በባንከ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ / ሲፒኦ (በጥሬ ገንዘብ)ማስያዝና ውል መፈፀም አለበት።
  14. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በሁለት ኮፒ የሚመለከታቸውን ሰነዶች በሙሉ በማድረግ ስርዝ ድልዝ በሌለበት ሁኔታ ማቅረብ አለባቸው።
  15. የጨረታ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ክፍት ሆኖ ቆይቶ በእለቱ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የጨረታ ሳጥኑ ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ይታሸጋል።
  16. የጨረታ ሳጥኑ በማግስቱ በ16ኛው ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአዲስ አበባ ግብርና ሚኒስቴር ቢሮ ከጧዋቱ በ3፡30 ሰዓት ይከፈታል።
  17. ተጫራቾች ቢገኙም ባይገኙም መ/ቤቱ ጨረታውን የሚከፍት ይሆናል።
  18. መ/ቤታችን ከሚገዛው እቃ 20% /ሃያ ፐርሰት መጨመር ወይም መቀነስ ይችላል።
  19. ማዕከሉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  20. በተጨማሪ ማስረጃ በስልክ ቁጥር 09-55/09-88-82-40-14 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

 

የአብክመ/ሰሜን ሸዋ ዞን መንዝ ጌራ ምድር ወረዳ

 

Save Tender