የአርሲ ዞን ኅብረት ሥራ ማስፋፊያ ኤጀንሲ ለ2017ዓ.ም ለአርሶ አደሩ የሚቀርብ የተለያየ የአፈር ማዳበሪያ በአዳማ፣ በኢተያ፤ በአርሲ ሮቤ እና ሌሙ ከተማ ከሚገኘው ማዕከላዊ መጋዘኖች በዞኑ ውስጥ ወደሚገኙ መሰረታዊ የኅብረት ሥራ ማህበራት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማጓጓዝ ይፈልጋል፡፡
በኦሮሚያ ክልላዊ መስተዳድር የአርሲ ዞን ኅብረት ሥራ ማስፋፊያ ኤጀንሲ
በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
የአርሲ ዞን ኅብረት ሥራ ማስፋፊያ ኤጀንሲ ለ2017ዓ.ም ለአርሶ አደሩ የሚቀርብ የተለያየ የአፈር ማዳበሪያ በአዳማ፣ በኢተያ፤ በአርሲ ሮቤ እና ሌሙ ከተማ ከሚገኘው ማዕከላዊ መጋዘኖች በዞኑ ውስጥ ወደሚገኙ መሰረታዊ የኅብረት ሥራ ማህበራት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማጓጓዝ ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም :-
- ተጫራቾች ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር ከፍለው ንግድ ፍቃዳቸውን ያሳደሱ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር TIN NO ፣ የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ ያላቸው እና በፌዴራል በክልል ወይም በዞን ገንዘብ ጽ/ቤት ወይም በግዥዎችና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ አቅራቢነት የምስክር ወረቀት /supplier list/ ያላቸው እና የሚነበብ ኮፒ ማቅረብ ያኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነድን የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ) ለአርሲ ዞን ገንዘብ ጽ/ቤት ሂሳብ ቁጥር 1071378041218 ሲንቄ ባንክ ገቢ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት እለት ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የስራ ቀናት ከዞኑ ህብረት ሥራ ማኅበራት ማስፋፊያ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 01 ድረስ በመቅረብ መውሰድ ይችላል፡፡
- ተጫራቾች ከግብር ሰብሳቢው መ/ቤት የዘመኑን ግብር አጠናቀው ለመክፈላቸው እና ጨረታ ለመሳተፍ የሚያስፈልጋቸውን ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ተጫራቾች ለዚህ ሰነድ የጨረታ ማስከበሪያ 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ) ብር በአቅራቢያ በሚገኙ የታወቀ ባንክ በክፍያ ማዘዣ (CPO) ብቻ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ያለምንም ማጓጓዣ አቅርቦት ችግር አስተማማኝ አቅም ያላቸውና በራሱ ቢያንስ 10 ተሳቢ መኪና ማቅረብ የሚችል የባለቤትነት ማረጋገጫ (ሊብሬ) ኮፒ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቾች ይህ የጨረታ ሰነድ ማስታውቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ የሚወዳደሩበትን የዋጋ ማቅረቢያ በመሙላት 1 ኦርጅናል እና 1 ኮፒ በተለያዩ ፖስታ በማሸግ ከላይ በተራ ቁጥር 1፣2፣3፣4 እና 5 ላይ የተጠየቁትን የሰነድ መስፈርቶች በመጨመር እስከ 15ኛው የሥራ ቀናት ማቅረብ የሚኖርባቸው ሲሆን ጨረታው 16ኛው የስራ ቀን ከቀኑ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ዕለት ከቀኑ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአርሲ ዞን ገንዘብ ጽ/ቤት አዳራሽ ይከፈታል፡፡
- ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
በኦሮሚያ ክልላዊ መስተዳድር የአርሲ ዞን ኅብረት ሥራ ማስፋፊያ ኤጀንሲ
