የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ የድሬዳዋ ወደብና ተርሚናል ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ለቢሮ አገልግሎት የሚውል ዴስክ ቶፕ ኮምፒውተር፣ ዩፒኤስ፣ፕሪንተር፣ ላፕቶፕ ኮምፒውተር እና ፎቶ ኮፒ ማሽን ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ድሬዳዋ ወደብና ተርሚናል ቅ/ጽ/ቤት
ብሄራዊ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ ቁጥር ድዳወተ/03/2017
የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ የድሬዳዋ ወደብና ተርሚናል ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ለቢሮ አገልግሎት የሚውል ዴስክ ቶፕ ኮምፒውተር፣ ዩፒኤስ፣ፕሪንተር፣ ላፕቶፕ ኮምፒውተር እና ፎቶ ኮፒ ማሽን ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ በዘርፉ የተሰማሩ ድርጅቶች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች በማሟላት መጫረት የሚችሉ መሆኑን ይገልጻል።
- በዘርፉ የተሰማሩ ድርጅቶች የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው የሚያሳይ መረጃ (Tax clearance)፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት እና የተጨማሪ እሴት ታክስ ሰርተፍኬት ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የተለያዩ ቴክኒካል ሰነዶችን እና ፋይናንሽያል ሰነድ በተለያየ ፖስታ በማሸግ አንድ ላይ ከአንድ ኮፒ ጋር መቅረብ አለበት::
- የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 50,000 /ሃምሳ ሺህ ብር/ በሲፒኦ ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ “የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ” በሚል ስም በማሰራት ከጨረታ ፖስታው ጋር በማቅረብ መጫረት ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ሰነዱን ለመግዛት የማይመለስ ብር 300 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ድሬዳዋ ወደብና ተርሚናል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት መልካ ጀብዱ አለፍ ብሎ በሚገኘው አዲሱ ህንጻ 2ኛ ፎት ላይ በሚገኘው የሀብት አስተዳደር ዋና ክፍል መውሰድ ይችላሉ።
- ጨረታው በኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ድሬዳዋ ወደብና ተርሚናል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት አዲሱ ህንጻ 2ኛ ፎት የካቲት 20 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ በ9፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት በ9፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ፖስታው ይከፈታል፡፡
- ከጨረታ መክፈቻው ቀንና ሰዓት በኋላ ዘግይቶ የሚመጣ የጨረታ ሠነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ስልከ ቁጥር ፡- 09-13-05-10-96
የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ድሬዳዋ ወደብና ተርሚናስ ቅ/ጽ/ቤት
