Tender Detail

Tender Details

  • Company የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍ/ቤት
  • Address ደቡብ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0462125584
  • Website
  • Deadline27 Feb 2025, 2:30 PM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Generators

የሲዳማ ብሔራዊ ከልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ለመ/ቤቱ አገልግሎት የሚውሉ ከዚህ በታች በሎት የተገለጹ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍ/ቤት


 

የጨረታ ማስታወቂያ 08/2017

 

የሲዳማ ብሔራዊ ከልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ለመ/ቤቱ አገልግሎት የሚውሉ ከዚህ በታች በሎት የተገለጹ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ሎት 1. ጀነሬተር

በዚህ መሠረት፡-

  1. በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያለው፤ የዘመኑን ግብር የገበረ፤ የቫት /VAT/ ተመዝጋቢነት ሰርቲፍኬት ያለው
  2. የግብር ከፋይ /TIN/ መለያ ቁጥር ያለው፤ የእቃና የአገልግሎት አቅራቢነት ሰርቲፍኬት ማቅረብ የሚችሉ ድርጅቶች
  3. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሰውን ማስረጃዎችን አሪጅናልና ኮፒ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  4. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15 ተከታታይ ቀናት ከላይ ለተገለጸው ሎት ሰነድ የማይመለስ ብር 100 ( አንድ መቶ) ብር ብቻ በሲዳማ ክልል ገቢዎች ባለስልጣን በተከፈተው ንግድ ባንከ አካውንት ቁጥር 1000347602028 በማስገባት እስሊፕ ይዞ ሲዳማ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ቢሮ ቁጥር 208 በመቅረብ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ።
  5. ተጫራቾች ለሚያቀርቡት የጨረታ ዋጋ ማስከበሪያ በCPO /BID BOND/ የ90 ቀን ለሎት ብር 10,000 (አስር ሺህ) ብር በጠቅላይ ፍርድ ቤት ስም በማሰራት ማቅረብ የሚችል፡፡
  6. ተጫራቾች የፋይናንሻል ዶክመንት ኦሪጅናል 1 እና 2 ኮፒ በተለያየ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ለጨረታ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ መከተት ይኖርባቸዋል፡፡ እንዲሁም ቴከኒካል ዶክመንት ኦሪጅናል 1 እና ኮፒ 1 በተለያየ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  7. ጨረታው በጋዜጣ ላይ ከወጣበት ተከታታይ ቀናት ቅዳሜና እሁድን ጨምሮ ከ15 ቀን በኋላ በ16ኛ ቀኑ 8፡30 ሰዓት ተዘግቶ 8፡45 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። ዕለቱ በዓል፣ ወይም የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተገለጸው ሰዓት ይከፈታል፡፡
  8. የጨረታ አሸናፊ ዕቃውን በራሱ ወጪ አጓጉዞ መጋዘን ማስገባት ይኖርበታል፡፡
  9. የጨረታው አሸናፊ በጨረታ መመሪያ መሠረት አሸናፊነቱ በማስታወቂያ ይገለጻል፡፡
  10. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 0462125584/ 0939126096

 

የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍ/ቤት

 

Save Tender