በፋና ቦሌ ሸማቾች ኃላ/የተ/የህ/ስራ/ማህበር በ2017 ዓ.ም በዓመት ውስጥ ሊገዛቸው ያሰባቸውን የተለያዩ ግብዓቶችን በትስስር ማዕከላትን ጨምሮ ጥቅል ግዥ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በፋና ቦሌ ሸማቾች ኃላ/የተ/የህ/ስራ/ማህበር በ2017 ዓ.ም በዓመት ውስጥ ሊገዛቸው ያሰባቸውን የተለያዩ ግብዓቶችን በትስስር ማዕከላትን ጨምሮ ጥቅል ግዥ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
|
ተ.ቁ |
የሎት ቁጥር |
የዕቃው ዝርዝር /ዓይነት/ |
|
1 |
ሎት 1 |
አትክልትና ፍራፍሬዎች |
|
2 |
ሎት 2 |
የበግ ስጋ አቅራቢዎች |
|
3 |
ሎት 3 |
እንስሳትና የእንስሳት ተዋጽኦ አምራቾችና አከፋፋዮች (ወተት፤ ቅቤ፤ አይብ እንቁላል እና አሳ) |
|
4 |
ሎት 4 |
አምራች ድርጅቶች (ምግብ ነክ፤ የጽዳት እቃዎች) |
|
5 |
ሎት 5 |
ፋብሪካዎች ምግብ ነክ፤ የጽዳት እቃዎች |
|
6 |
ሎት 6 |
አስመጪዎች |
|
7 |
ሎት 7 |
ጅምላ ነጋዴዎች |
|
8 |
ሎት 8 |
ህብረት ስራ ዩኒየኖች |
ስለዚህ ከዚህ በታች ያሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ህጋዊ ተጫራቾች ቀርበው መወዳደር ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው፣ ቫት ተመዝጋቢ የሆኑ፣ የምግብና መድኃኒት ቁጥጥር ባለሥልጣን ሰርተፍኬት ያላቸውና በፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡና ከድረ ገጽ ላይ የአቅራቢነት ማስረጃ ኮፒ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችላቸው ከግብር ሰብሳቢ መ/ቤት የተሰጠ ክሊራንስ ደብዳቤ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ጨረታው ከመከፈቱ በፊት የሚወዳደሩባቸውን እቃዎችና ናሙና በዝርዝር ማቅረብ አለባቸው::
- በዓመት ውስጥ ሊገዙ የታሠቡትን ግብዓቶች ዓመታዊ ትስስር ይፈጽማል፡፡
- ተጫራቾች በአማርኛ ቋንቋ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ የሥራ ቀናት በየሎት የማይመለስ የኢትዮጵያ ብር 150 /አንድ መቶ ሃምሳ ብር/ 17/18 መዝናኛ ማዕከል ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ውስጥ ፋይናንስ ቢሮ ሰነድ በመግዛት ደረሰኝ መውሰድ ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ያሸነፉትን ዕቃዎች ከአጠቃላይ ዋጋ ብር 10 % የውል ማስከበሪያ በማስያዝ ከድርጅቱ ጋር የግዥ ውል ስምምነት መፈጸም ይኖርባቸዋል፡፡
- ፋና ቦ/ሸማቾች ኃላ/የተ/የህ/ስራ ማህበር የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ማሳሰቢያ:- ተጫራቾች ተጨማሪ መረጃ ከፈለጉ በአካል ፋና ቦሌ ሸ/ኃ/የተ/የህ/ስራ ማህበር 17/18 ህ/ል/ማዕከል ግቢ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ድረስ በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 09-34-02-68-75/09-52-29-29-29 መረጃ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
አድራሻ፡- 22 አውራሪስ ሆቴል ዝቅ ብሎ 17/18 ህ/ል/ማዕከል ውስጥ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ቢሮ 1/የተ/የህ/ሥራ ማህበር
ፋና ቦሌ ሸማቾች ኃላ/የተ/የህ/ሥራ ማህበር
