የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልላዊ መንግስት መንገዶች ባለሥልጣን ዋና መ/ቤት በተለያዩ ፕሮጀክቶች እና ጥገና ጽ/ቤቶች ለሚያከናውናቸው የመንገድ ግንባታ እና ጥገና ሥራ አገልግሎት የሚውል በሎት 1 የገልባጭ መኪናዎችን ከነሎደሩ፣ በሎት 2 ዶዘር፣ ኤክስካቫተር፣ ግሬደር እና ሮለር በጨረታ አወዳድሮ ለመከራየት ይፈልጋል፡፡
South West Ethiopia Roads Authority (የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን)
ለ3ኛ ጊዜ የወጣ የጨረታ ቁጥር 008/2017
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልላዊ መንግስት መንገዶች ባለሥልጣን ዋና መ/ቤት በተለያዩ ፕሮጀክቶች እና ጥገና ጽ/ቤቶች ለሚያከናውናቸው የመንገድ ግንባታ እና ጥገና ሥራ አገልግሎት የሚውል በሎት 1 የገልባጭ መኪናዎችን ከነሎደሩ፣ በሎት 2 ዶዘር፣ ኤክስካቫተር፣ ግሬደር እና ሮለር በጨረታ አወዳድሮ ለመከራየት ይፈልጋል፡፡
በዚሁም መሰረት ከዚህ በታች በተዘረዘሩት ዝርዝር መሰረት አቅራቢዎችን ይጋብዛል፡-
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የሚያስችለውን የዘመኑ ግብር የተከፈለበትን ከሚፈለገው አገልግሎት ጋር የተዛመደ የንግድ ሥራ ፈቃድ ወይም የአገልግሎት ሥራ ፈቃድ ፣ የአቅራቢነት ምስክር ወረቀት፣ ተጨማሪ እሴት ታክስ፣ የንግድ ምዝገባ ሰርተፍኬት ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (TIN NO) እና በጨረታ ለመሳተፍ ከሀገር ውስጥ ገቢ ቢሮ የድጋፍ ደብዳቤ ከጨረታ ሰነዳቸዉ ጋር አያይዞ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ዋጋቸዉን በታሸገ ኤንቨሎፕ የፋይናንሻል እና ቴክኒካል ፕሮፖዛሉን በተለያዬ ፖስታ በማድረግ አንድ ዋና እና ሁለት ኮፒ ኦርጅናል እና ኮፒ›› በማለት እና የጨረታ ማስከበርያዉንም ለእያንድንዱ ሎት በተለያዬ ፖስታ ለየብቻ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ) ብር በባለስልጣን መ/ቤቱ የባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000642058936 በማስገባት ባንክ ደረሰኝ በመያዝ ከባለስልጣን መ/ቤቱ ግዥ እና ንብረት አስተዳደር ኬዝ ቲም ቢሮ መዉሰድ ይችላሉ።
- የጨረታው አሸናፊ የሚወሰነው በጨረታ ሰነዱ ውስጥ በተመለከቱት መስፈርቶች መሰረት ሲሆን ጨረታው ዜግነትን ሳይመለከት ለማንኛውም አቅራቢ ክፍት ነው ::
- አቅራቢዎች ጨረታውን ለዚህ ተግባር በተዘጋጀ ሳጥን ገቢ የሚያደርጉበት ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛ ቀን ሲሆን ጨረታው በ16ኛ ቀን 3:00 ተዘግቶ በዛዉ ቀን 3፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ይከፈታል ፡፡ እለቱ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል ፡፡
- ተጫራቾች የጠቅላላ ዋጋ 1% የጨረታ ማስከበሪያ በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም ሲፒኦ (CPO) በየሎት ለይተው ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር በማያያዝ ማቅረብ ይኖርባቸዋል :: ከዚህ ውጭ በኢንሹራንስ ወይም በሌላ መልክ የሚቀርብ የጨረታ ማስከበሪያ ተቀባይነት የለውም ።
- ተጫራቾች በጨረታው ደንብና መመሪያ መሰረት ጨረታቸዉን ማቅረብ አለባቸዉ ከጨረታ ደንብና መመሪያ ውጭ የሚቀርብ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም ::
- ተጫራቾች ከ2015 ዓ.ም ጀምሮ በተመሳሳይ ዘርፍ ከሰሩበት የመንግስት መ/ቤት ቢያንስ ሁለት የመልካም ስራ አፈፃፀም ከጨረታ ሰነዳቸዉ ጋር አያይዞ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል::
- መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
- ለበለጠ መረጃ ተጫራቾች የሚከተለውን አድራሻ መጠቀም ይችላሉ፡
በምዕራብ ኦሞ ዞን ጀሙ ከተማ በሚገኘዉ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ከልል መንግስት መንገዶች ባለስልጣን ዋና መ/ቤት በግብዓት አቅርቦትና አስተዳደር ዘርፍ ግዥና ንብረት አስተዳደር ኬዝ ቲም ቢሮ በአካል በመቅረብ ማነጋገር ወይም በስልክ ቁጥር 0474527941 0474527727 ደዉለዉ ማነጋገር ይቻላል::
ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት መንገዶች ባለስልጣን ዋና መ/ቤት
ምዕራብ ኦሞ ዞን/ጀሙ ኢትዮጵያ
