ሪፍት ቫሊ ችልድረን ኤንድ ውመን ዴቨሎፕመንት ኦርጋናይዜሽን በድርጅቱ የተለያዩ ቅርንጫፍ ውስጥ የሚገኙትን የተለያዩ ሞተር ሳይክሎችንና ፎር ዊል ቢ-ግሬድ ባይክ (Four Wheel B-grade bike) (በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
ሪፍት ቫሊ ችልድረን ኤንድ ውመን ዴቨሎፕመንት ኦርጋናይዜሽን በድርጅቱ የተለያዩ ቅርንጫፍ ውስጥ የሚገኙትን የተለያዩ ሞተር ሳይክሎችንና ፎር ዊል ቢ-ግሬድ ባይክ (Four Wheel B-grade bike) (በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ተጫራቾች:-
- ማንኛውም ተጫራች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ሞተር ሳይክሎቹ በሚገኙበት አድራሻ በሻሸመኔ ሲ.ዲ.አይ (CDI) ቢሮ መልካ ኦዳ ሆስፒታል ፊት ለፊት ግቢ ውስጥ እና በባቱ ከተማ ፎር ዊል ቢ-ግሬድ ባይከ (Four Wheel B-grade bike) መመልከት የሚችሉ ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች የሚገዙትን ሞተር ሳይክል ጠቅላላ ዋጋ 20 በመቶ (20%) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) አሰርተው ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ የሚዘጋጀው የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ከአዲስ አበባ ከተማ ውጭ ከሆነ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንከ ቅርንጫፍ ብቻ መሆን ይኖርበታል፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትናው ለአሸናፊዎች ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር የሚታሰብ ሲሆን ለተሸናፊዎች የጨረታው ውጤት እንደፀደቀ ይመለስላቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ሞተር ሳይክሎችን እና ፎር ዊል ቢ-ግሬድ ባይኮችን ዝርዝር የያዘው ሰነድ ላይ ተጫራቹ የሰጠው ዋጋ በሚለው አምድ /column/ ስር የሚገዙበትን ዋጋ በእኅዝና በፊደል ያለ ስርዝ ድልዝ ገልፀው በታሸገ ኤንቨሎፕ/ ፖስታ ሻሸመኔ ሰ.ዲ.አይ (CDI) ቢሮ መልካ አዳ ሆስፒታል ፊት ለፊት በሚገኘው የድርጅቱ ቅርጫፍ ጽ/ቤት አስተዳደርና ፋይናንስ መምሪያ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡ ፡ ነገር ግን የሚሰጡት ዋጋ ላይ ስርዝ ድልዝ ካለ ከጎኑ በተጫራቹ ወይም በተወካዩ መፈረም አለበት፡፡
- ተጫራቶች ጨረታው በተለያዩ የማስታወቂያ ሰሌዳዎችና በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከተለጠፈበት ቀን ጀምሮ ባሉት 07 (ሰባት) ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ የጨረታውን ሰነድ ማስገባት አለባቸው::
- አሸናፊ ተጫራቾች ጨረታውን ማሸነፋቸው ከተገለፀላቸው ቀን ጀምሮ በ03 ቀናት ውስጥ ገንዘቡን ገቢ በማድረግ በ5 ቀናት ውስጥ ንብረቱን የመረከብ ግዴታ አለባቸው፡፡ ይህ ካልሆነ ያስያዙት ገንዘብ ለድርጅቱ ገቢ ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች ዝርዝር መረጃ የያዘ የተጫራቾች መመሪያ እና የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ለአንድ ሞተር ሳይክል ወይም ፎር ዊል ቢ-ግሬድ ባይክ የማይመለስ 300 ብር (ሦስት መቶ ብር) እየከፈሉ ባሉት 07 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ እስከ ሰባተኛው ቀን 6፡30 ሰዓት ድረስ መግዛት ይችላሉ፡፡ ለተጨማሪ ሞተር ሳይክል ወይም ፎር ዊል ቢ-ግሬድ ባይክ መጫረት ከፈለጉ ተጨማሪ ሰነድ መግዛት አለባቸው።
- የጨረታ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ወይም በተለያዩ ማስታወቂያ ሰሌዳዎች ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 07 (ሰባት) የሥራ ቀናት ክፍት ሆኖ በሰባተኛው ቀን ከቀኑ 9፡30 ሰዓት ተዘግቶ በዚያው ቀን 10፡00 ሰዓት ተጫራቾቹ ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ የሻሸመኔ ቅርንጫፍ የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች ስለ አሻሻጡ ዝርዝር ሁኔታ ከጨረታ ሰነድ ጋር ከተያያዘው የተጫራቾች መመሪያ ላይ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ድርጅቱ ላሻሻጡ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፈል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር ፡- 09-20-52-37-34/ 09-11-23-65-37 መደወል የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
ሪፍት ቫሊ ችልድረን ኤንድ ውመን ዴቨሎፕመንት ኦርጋናይዜሽን
