በኢትዮጵያ ጉምሩከ ኮሚሽን የሞጆ ቅ/ጽ/ቤት በግዥ መለያ ቁጥር ECC-MOJ/NCB/06/2017 በግልፅ ጨረታ የግዥ ዘዴ የሚከተሉትን አገልግሎት ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር ECC-MOJ/NCB/06/2017
በኢትዮጵያ ጉምሩከ ኮሚሽን የሞጆ ቅ/ጽ/ቤት በግዥ መለያ ቁጥር ECC-MOJ/NCB/06/2017 በግልፅ ጨረታ የግዥ ዘዴ የሚከተሉትን አገልግሎት ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡
* ሎት 1 - የተለያዩ አይነት የጭነት አገልግሎት ግዥ
በጨረታ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ድርጅቶች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፣
- ከሚያቀርቡት አገልግሎት ጋር የተዛመደ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆኑ የሚያረጋግጥ ማስረጃ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (Tin Number) ማስረጃዎችን ማቅረብ የሚችሉ
- ግብር የመክፈል ግዴታቸውን የተወጡ መሆኑን የሚያረጋግጥ በግብር አስገቢው ባለስልጣን የተሰጠ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
- ለተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ሃምሳ) ብር በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጨረታው መክፈቻ ቀን ድረስ መሿለኪያ አካባቢ ይርጋ ሃይሌ ፕላዛ ከሚገኘው የኮሚሽኑ ዋ/መ/ቤት የግዢ ቡድን አራተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 401 በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ቅዳሜን እንደ ስራ ቀን ተቆጥሮ ተከታታይ 15 የስራ ቀናት ድረስ ከጠዋት 4፡00 ሰዓት በፊት ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው በዚሁ እለት ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት በኮሚሽኑ ዋ/መ/ቤት የግዢ ቡድን ሶስተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 301 ቢሮ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል::
- ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡
- ሰነዱ በሚላክበት ወቅት ስልጣን ባለው አካል መፈረምና የድርጅቱ ማህተም መደረግ አለበት ነገር ግን የሚፈርመው አካል ተወካይ ከሆነ የውክልና ማስረጃው መያያዝ አለበት፡፡
- አንዱ ተጫራች ባቀረበው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችልም፡፡
- የጨረታው አሸናፊ የመልካም ስራ አፈፃፀም ዋስትና 10% (አስር በመቶ) CPO ወይም ባንክ ጋራንቲ በማስያዝ ከመ/ቤቱ ጋር ውል ይፈራረማል፡፡
- ተጫራቾች በሚወዳደሩባቸው ሁሉም ዕቃዎች ላይ የጨረታ ሰነዱን ሲያስገቡ ናሙናዎቹንም ለግዥ ክፍል ማስረከብ አለባቸው፡፡ ናሙና ያላቀረበ ድርጅት ለውድድር አይቀርብም፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ስልክ ቁጥር 0222361314 09240770780910901112
በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የሞጆ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት
