ገዳ ትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ አ.ማ ሞጆ በሚገኘው የድርጅቱ ዎርክ ሾፕ ውስጥ ያሉትን የተለያዩ ያገለገሉ ጎማዎችን ፣ የተቃጠሉ ዘይቶችን ፤ ከመነዳሪ እና ፍላፖችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
የሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር (Gada/NCB/07/2017)
ገዳ ትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ አ.ማ ሞጆ በሚገኘው የድርጅቱ ዎርክ ሾፕ ውስጥ ያሉትን የተለያዩ ያገለገሉ ጎማዎችን ፣ የተቃጠሉ ዘይቶችን ፤ ከመነዳሪ እና ፍላፖችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል። ስለሆነም በጨረታው መወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተመለከቱትን መስፈርቶች በማሟላት መጠዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን ::
- ኢትዮጵያዊ የሆነ/የሆነች እና የታደሰ የኗሪነት መታወቂያ ያለው ወይም ያላት እና በማንኛውም ንግድ ስራ ላይ የተሰማራ ወይም የተሰማራች መሆን አለበት/አለባት፤
- ማንኛውም ተወዳዳሪ ተጫራች የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 16 ቀን አየር ላይ የሚውል ሲሆን ሰንጋ ተራ ንግድ ስራ ኮሌጅ ፊት ለፊት ቢፍቱ አዱኛ ህንጻ 12ኛ ፎቅ ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 11፡00 በመምጣት የማይመለስ 100 (አንድ መቶ) ብር በመክፍል የጨረታ ሰነዱን በመግዛት መወዳደር ይችላሉ።
- ማንኛውም ተጫራች በገዛው የጨረታ ሰነድ ላይ ክብ ማህተም ወይም በመፈርም በሰም በታሸገ ፓስታ ማቅረብ ይኖርበታል።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ አጠቃላይ ከተወዳደሩበትን ዋጋ 2% በ ሲ.ፒ.ኦ ማቅረብ ያለባቸው ሲሆን የሞሉትን ጨረታ እንዲሁም ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በአንድ ላይ በፖስታ በማሸግ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የጨረታ ሰነድ የገዙ ተወዳዳሪውች የገዙትን ሰነድ እና ደረሰኝ በመያዝ እቃዎችን ሞጆ በሚገኘው የድርጅቱ የተሽከርካሪ ማቆሚያ ግቢ ውስጥ ማየት ይቻላል።
- የጨረታ አሸናፊነቱ ከተረጋገጠ ቀን ጀምሮ ባሉት 5 ተከታታይ የስራ ቀናት አጠቃላይ ያሸነፉበትን እቃ ሙሉ በሙሉ በመክፈል እቃውን ከጊቢ ማውጣት አለባቸው።
- ተጫራች በሚያቀርቡት ዋጋ የጨረታ መግቢያ ሰዓት ከተጠናቀቀ በኋላ ማሻሻያ ማድረግ እና እራሳቸውን ከጨረታ ማግለል አይቻልም
- ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ16 ቀን አየር ላይ የሚውል ሆኖ በ16ኛው ቀን በ8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዛው እለት 8፡30 ላይተጫራቾች እና ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ይሆናል።
- ንብረቶቹ የሚገኙበት ቦታ ሞጆ ይገኛሉ
- የጨረታ መከፈቻ ቀናት ቅዳሜ እና እሁድ እንዲሁም በበዓላት ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል።
- ድርጅቱ የተሻለ አማሪ ጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ ፡- ሰንጋ ተራ ንግድ ስራ ኮሌጅ ፊት ለፊት ቢፍቱ አዱኛ ህንጻ 12ኛ ፎቅ
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 011-558-25-19
ገዳ ትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ አ.ማ
