የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት የወላይታ ዞን አረካ ከተማ ፋይ/ጽ/ቤት በ2017 በጀት ዘመን በማዘጋጃ ቤት መደበኛ ፕሮግራም የሚሠሩ የኮሪደር ልማት የግንባታ ዕቃዎች ግዥ እና የከተማው ውስጥ ለውስጥ መንገድ ከፈታ ሥራ የማሽነሪ ኪራይ አገ/ት ግዢ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በወላይታ ዞን አረካ ከተማ አስ/ር ፋይናንስ ጽ/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት የወላይታ ዞን አረካ ከተማ ፋይ/ጽ/ቤት በ2017 በጀት ዘመን በማዘጋጃ ቤት መደበኛ ፕሮግራም የሚሠሩ የኮሪደር ልማት የግንባታ ዕቃዎች ግዥ እና የከተማው ውስጥ ለውስጥ መንገድ ከፈታ ሥራ የማሽነሪ ኪራይ አገ/ት ግዢ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በዚህ መሠረት :-
lot 1 ለኮሪደር ልማት የግንባታ ዕቃዎች (materials) ግዥ
lot 2 የከተማው ውስጥ ለውስጥ መንገድ ከፈታ ሥራ የማሽነሪ ኪራይ አገ/ት ግዥ
በዚህ መሠረት ተወዳዳሪዎች ማሟላት የሚጠበቅባቸው
- በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያለው
- የ2017 ዓ.ም ግብር ከፍሎ የንግድ ፈቃድ ያሳደሰ
- የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያለው
- ቲን ሠርቴፊኬት ያለው
- ቫት ተመዝጋቢ የሆነ
- በOnline አቅራቢነት E-GP የተመዘገበ እና የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ብር ለሎት-1 = 60,0000 (ስልሳ ሺህ ብር) ለLot 2 = 50,000 (ሃምሳ ሺህ ብር ፣ በባንከ የተረጋገጠበት ቼክ (ሲ.ፒ.ኦ) በጥሬ ገንዘብ በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንከ ዋስትና በባንክ የተረጋገጠ ሌተር ኦፍ ክሬዲት ማቅረብ ይኖርባችኋል፡፡
- ተጫራቹ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ የማይመለስ ብር 300.00 /ሶስት መቶ ብር ብቻ/ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ከአረካ ከተማ ፋይናንስ ጽ/ቤት በፑል ማዕከል መግዛት የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን የአንዱንና ጠቅላላ ዋጋ በጨረታ ሰነድ ላይ በመሙላት ለዚሁ አገልግሎት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በሰም የታሸገ ፖስታ አንድ ኦሪጂናል እና ሁለት ኮፒ በአንድ እናት ፖስታ ውስጥ በማሸግ ማቅረብ የሚቻል ሲሆን ጨረታው የሚከፈተው በ16ኛው ቀን ዕለቱ የሥራ ቀን ከሆነ ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጎ በዕለቱ 4፡30 ይከፈታል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ተጫራቾች ያለመገኘታቸው የጨረታ ሂደቱን አያስተጓጉልም፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር ፡- 0465520800/0241/0913055185 ማነጋገር ይችላሉ
በወላይታ ዞን የአረካ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት
